በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የአየር ክልል ለማንኛውም በረራ የተዘጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 26 ቀን 20…

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የአየር ክልል ለማንኛውም በረራ የተዘጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 26 ቀን 20…

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የአየር ክልል ለማንኛውም በረራ የተዘጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከጥቅም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በሰሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የዓለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት የተዘጉ መሆኑን ለሁሉም ሃገራት ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሰሜን የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የአየር ክልል ለማንኛውም በረራ የተዘጋ በመሆኑ ይህን ማሳሰቢያ ተላልፎ በረራ የሚፈጽም ማንኛውም አውሮፕላን እንዳይኖር አሳስቧል ሲል ዋልታ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply