በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት የፈጸሙ እና በማይካድራው ጭፍጨፋ የተሳተፉ አካላት በቀጣይ ሳምንታት ለህግ እንደሚቀርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ  አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  የ…

በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት የፈጸሙ እና በማይካድራው ጭፍጨፋ የተሳተፉ አካላት በቀጣይ ሳምንታት ለህግ እንደሚቀርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የ…

በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት የፈጸሙ እና በማይካድራው ጭፍጨፋ የተሳተፉ አካላት በቀጣይ ሳምንታት ለህግ እንደሚቀርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጁንታው በፈጸመውን ጥቃት አማካኝነት ተገዶ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ መግባቱ ይታወሳል። ይህንን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎም በክልሉ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለማጣራት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ እና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ምርምራ እያካሄዱ ይገኛሉ ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቋል። ተቋማቱ በምርመራቸውም የደረሱባቸውን ግኝቶች ይፋ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሷል። ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ሲባልም በተቋማቱ ግኝት መሰረት አስፈላጊው እርምጃ ሁሉ ተወስዷል ብሏል መግለጫው። በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት የፈጸሙ እና በማይካድራው ጭፍጨፋ ላይ የተሳተፉ አካላት በሙሉ በቀጣይ ሳምንታት ለህግ እንደሚቀርቡም ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ያስታወቀው። መንግስት ለህግ የበላይነትና ተጠቀያቂነት ካለው ቁርጠኝነት የተነሳ፤ በኢትዮጵያ ያሉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተገቢ ተቋማትና ባለስልጣናት ምርመራውን ያከናውናሉ ሲልም ነው ያረጋገጠው። ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሟል የሚሉትንና በአክሱም ከተማ ተፈጽሟል ስለተባለው ሁኔታ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አማካኝነት ተገቢው ምርመራ እየተከናወነ እንደሆነ እናውቃለን ሲልም ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በመግለጫው ያስታወቀው። ኮሚሽኑ ይህንን ምርመራ ዓለም አቀፍ ከፍተኛ ባለሙያዎችን በመቅጠርና በትብብር ጭምር እየተከታተለው እንደሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያው አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስና ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ምርመራ እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሶ፤ ተቋማቱ የመጨረሻውን ግኝታቸውን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ መንግስትም በዚህ ግኝት ላይ በመመስረት በህግ አግባብ የራሱን እርምጃ እንደሚወስድ አረጋግጧል። ግጭት ባለበት በየትኛውም አካባቢ ያልተጠበቁ አሳዛኝ ነገሮች ሊከሰቱ የሚችሉ ቢሆንም፤ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለአደጋ የሚያጋልጡ ማንኛውንም አይነት ድርጊቶች እንድማይታገስ አረጋግጧል ሲል ኢ ፕ ድ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply