በሰሜን ካሊፎኒያው ከባድ ዝናብና ነፋስ ሁለት ሰዎች ሞቱ

https://gdb.voanews.com/03370000-0aff-0242-4a18-08daefebebb9_w800_h450.jpg

ሰሜን ካሊፎርኒያን ትናንት ሀሙስ የመታው ኃይለኛው ዶፍ ዝናብ እና ከባድ ነፋስ በተገነደሰ ዛፍ ቤት ውስጥ እንዳለ ህይወቱን ያጣውን ህጻን ልጅ ጨምሮ ሁለት ሰዎችን መግደሉ ተሰማ።

ከባድ ነፋስና ዝናብ የቀላቀለው የአየር ጠባይ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችና የተወሰኑ የንግድ ድርጅቶችን ያለ ኤሌክትሪክ ኃይል ያስቀረ ሲሆን በባህሩ ዳርቻ ባሉ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ መፍጠሩ ተመልክቷል።

“ፓይን አፕል” የሚል ስያሜ የተሰጠው ከባዱ ዝናብና ነፋስ ከሃዋዪ ደሴት አቅጣጫ ተነስቶ ወደ ምዕራብ የባህር ዳርቻ የዘለቀ ሲሆን “ቦምብ ሳይክሎን” የተባለውንና ቶሎ ቶሎ የሚወርደውን ከፍተኛ የአየር ግፊት የሚያዟዙር መሆኑ ተነግሯል።

በሳን ፍራንሲስኮ አካባቢ ያለው ነፋስ በሰዓት 160 ኪሎ ሜትሮች በላይ መጓዙ የተነገረ ሲሆን ከሳን ፍራንሲስኮ የሚነሱ ከ70 በላይ የሚሆኑ በረራዎች መቋረጣቸው ተዘግቧል።

በአካባቢው በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ተጨማሪ ዝናብና ነፋስ ይኖራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply