በሰሜን ወሎ፣ በዋግኸምራ፣ በሰሜን ጎንደር እንዲሁም በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች እና በአፋር በአሸባሪው ትሕነግ ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲደረግ ሰል…

በሰሜን ወሎ፣ በዋግኸምራ፣ በሰሜን ጎንደር እንዲሁም በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች እና በአፋር በአሸባሪው ትሕነግ ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲደረግ ሰልፈኞች ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ወሎ፣ በዋግኸምራ፣ በሰሜን ጎንደር እንዲሁም በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች አሸባሪውና ወራሪው የትሕነግ ቡድን በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የፈፀመውንና እየፈፀመ ያለውን ጥቃት ያወገዙ ሰላማዊ ሰልፈኞች ለመንግስትና ለአለም ዓቀፍ ረጅ ድርጅቶች የድጋፍ ጥሪ አድርገዋል። መንግስት በአስቸኳይ በወረራ በተያዙ አካባቢዎች ያሉ ወገኖቻችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ነጻ ለማውጣት እንዲሰራ የጠየቁት ሰልፈኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ አለም ዓቀፍ ተቋማት በር ድረስ በማቅናት አድሎአዊ አሰራራቸውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል። ሰልፈኞቹ አለም ዓቀፍ ተቋማት ላለፉት ስምንት ወራት መቀሌን ጨምሮ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እንዳደረሱት ሁሉ በግድያ፣ በአፈና እና በረሃብ እየተሰቃዩ ላሉ አማራዎችና አደኘፋሮችም ሊደርሱ ይገባል ብለዋል። መንግስትና አለም ዓቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ቸልተኝነታቸውንና ሴራቸውን ወደ ጎን በመተው በአስቸኳይ ለሰብአዊነት እንዲደርሱ ተጠይቋል። መስከረም 11 ቀን 2014 ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የተለያዩ አለም ዓቀፍ ረጅ ድርጅቶች በሚገኙበት አካባቢ በመንቀሳቀስ በተደረገው ሰልፍ የሰልፉ አስተባባሪዎች ለተቋማቱ አመራሮች ገብተው መልዕክታቸውን በደብዳቤ አስደግፈው አድርሰዋል፤ የተሳካ ውይይትም አድርገዋል። ሰላማዊ ሰልፉ የተካሄደው በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ደንበል አካባቢ በመገናኘት ሲሆን በእለቱም አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች UNICEF እና WFP በር ላይ ሰልፈኞች መልዕክታቸውን አስተጋብተዋል። በመቀጠልም አለም ዓቀፍ የቀይ መስቀል ድርጅትና ሌሎች ተቋማትን ለመድረስ ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች የመጡ ሰብአዊነት ይገደናል የሚሉ ተሳታፊዎች አቅንተዋል። በሰልፉ ላይ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ በርካታ የሚሆኑ የሰሜን ወሎ፣ የዋግኸምራ፣ የሰሜን ጎንደርና ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች የመጡ ወገኖች ተሳትፈውበታል። አሚማ በስፍራው ተገኝቶ ሰላማዊ ሰልፉን ተከታትሏል፤ የሰልፉ አስተባባሪዎችንና ተሳታፊዎችንም አነጋግሯል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply