በሰሜን ወሎ ዋድላ ወረዳ በዋሻ ውስጥ ሲኖሩ ለነበሩ ሰዎች የቤት መስሪያ ቆርቆሮ ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በ…

በሰሜን ወሎ ዋድላ ወረዳ በዋሻ ውስጥ ሲኖሩ ለነበሩ ሰዎች የቤት መስሪያ ቆርቆሮ ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ወሎ ዋድላ ወረዳ በጦርነቱ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ቤታቸው ለፈረሰባቸው 28 አባዎራወች የቤት መስሪያ ቆርቆሮ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል። ድርጅቱ 600,000 ብር /ስድስት መቶ ሺ ብር / ወጭ የተደረገበት ለ1 አባወራ 42 የቤት ቆርቆሮ በድምሩ 1,176 የቤት መስሪያ ቆርቆሮ ነው ድጋፍ ያደረገው። ይሄ ስራ እንዲሳካም በገንዘብ የደገፉ በካናዳ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ (ECNAS) እና በአሜሪካ ዋሽንግተን እስቴት ሲያትል ግብረሀል መሆናቸው ተገልጧል። ድጋፍ በተደረገላቸው ወገኖች ስም ወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት ከልብ ምስጋናውን አቅርቧል። የዋድላ ወረዳ በትግራይ ወራሪ ሀይል ለ5 ወር የተያዘ እና ለ5 ጊዜ ከፍተኛ ጦርነት የተደረገበት ቦታ በመሆኑ የብዙ ንፁሃን ህይወት የጠፋበት እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ ውድመት የደረሰበት ሲሆን በወረዳው የወደሙ ቤቶች አጠቃላይ ቁጥር 2,776 ቤቶች ሲሆኑ በአንድ ቀበሌ ብቻ በ017 ከወደሙ 360 ቤቶች መካከል 180 የሚሆኑት ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል። በዚህም ነዋሪዎቹ መጠለያ በማጣት እስከ አሁን ድረስ በዋሻ ውስጥ ለመኖር ተገደዋል ያለው ወሎ ቤተ አምሐራ የልማትና የበጎ አድራጎት ድርጅት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን መጭው የክረምት የዝናብ፣ የብርድ ጊዜ ከመምጣቱ በፊት እነዚህን ወገኖች መጠለያ እንዲያገኙ መንግስት እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥረት እንዲያደርግ ሲልም ጥሪ አቅርቧል። ወሎ ቤተ አምሐራ የልማትና የበጎ አድራጎት ድርጅት በወሎ ብሎም በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ፈጥኖ በመድረስና በመደገፍ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply