You are currently viewing በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ድሬ ሮቃ ጃራ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች መንግስት በርሃብ እንድንሞት ፈርዶብናል ሲሉ አማረሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም…

በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ድሬ ሮቃ ጃራ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች መንግስት በርሃብ እንድንሞት ፈርዶብናል ሲሉ አማረሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም…

በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ድሬ ሮቃ ጃራ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች መንግስት በርሃብ እንድንሞት ፈርዶብናል ሲሉ አማረሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ድሬ ሮቃ ጃራ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው የሚኖሩት የራያ ተፈናቃዮች የምግብ እጥረት እየገጠማቸው በመሆኑ መንግስት በርሃብ እንድንሞት ፈርዶብናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በማንነታቸው ምክንያት ከአምስት ወረዳዎች ተፈናቅለው በጃራ መጠለያ የሚኖሩት ተፈናቃዮች ከሚኖሩበት ቤታቸው ያለምንም ገንዘብና ምግብ ተሰደው ቆቦ ከተማ እያሉ እየለመኑም ቢሆን ምግብ ያገኙ እንደነበር ተናግረዋል። መንግስት አሁን ወደአለንበት መጠለያ ጣቢያ ካመጣን በኋላ የምግብ እና የመጠለያ ችግር ገጥሞናል ይላሉ። ተፈናቃዮቹ ለጁንታ ተሠልፈን ወደ ወገናችን አፈሙዝ አናዞርም ብለን በመሠደዳችን መንግስት ሊደርስልን ይገባል ጦርነቱን በአጭር ጊዜ በመቋጨት ወደ አካባቢያችን ይመልሰን ሲሉ ብሶታቸውን ተናግረዋል፡፡ ህፃናት በሙቀትና በርሀብ ችግር ላይ በመሆናቸው ለህፃናት መብት እቆማለሁ የሚል ድርጅት እና መንግስት አፈጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር በመጠለያ ጣቢያው የምግብ አቅርቦት እጥረት መኖሩን አረጋግጠው ችግሩ የተከሰተው የፌደራል መንግስትና ረጅ ድርጅቶች ቃል በገቡት መሠረት እርዳታውን ማቅረብ ባለመቻላቸው ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አሁን ባለው ተጨባጭ መረጃ ከ25 ሺህ በላይ ተፈናቃይ በጃራ መጠለያ ሲኖሩ ከነዚህም ውስጥ 4 ሺህ ብቻ የሚሆኑት በጊዚያዊ መጠለያ የሚኖሩ ሲሆን ሌሎቹ ግን በዛፍ ጥላ ያሉ በመሆኑ በክረምት ወራትም የከፋ ችግር እንደሚገጥም ለፌደራል አደጋ ስጋት ችግሩን ብናሳውቅም መፍትሄ አላገኘንም፤ ሰዉ በምግብ እጥረት እየተሰቃየ ነው ብለዋል፡፡ የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply