You are currently viewing በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ላይ አሁንም የመንግስት ጨቋኝ አሰራሩን ቀጥሎበታል ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ።         አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ሀምሌ 19/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ…

በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ላይ አሁንም የመንግስት ጨቋኝ አሰራሩን ቀጥሎበታል ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 19/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ…

በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ላይ አሁንም የመንግስት ጨቋኝ አሰራሩን ቀጥሎበታል ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 19/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ በውስጥ ከተላኩለት መረጃዎች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል። በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ላይ አሁንም የመንግስት ጨቋኝ አሰራሩን ቀጥሎበታል። ግንቦት 15/2015 ዓ.ም ላብ አደሮችን (የቀን ሰራተኞች) ተሰባስበው ከሚያሰሯቸው አካላት ጋር ለመገናኘት በተለምዶ ቁም ቁም ተራ ወይም ወዛደር ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የእለት ተእለት ኑሯቸውን ለማሸነፍ እና ቤተሰናቸውን ለማስተዳደር ከሚተጉ የቀን ሰራተኞች በአካባቢው ለአብይ አህመድ አሽከር ካቢኔ ታዛዥ የሆኑ የተመረጡ ታጣቂ የሚሊሻና የፖሊስ አባላት አማካኝነት ከ130 ያላነሱ የቀን ሰራተኞችን በትጥቅ በማስፈራራት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸው እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ ካሰሩ በኋላ የ100 ልጆችን መታወቂያ በመቀማት ከሰዓት ለቀዋቸዋል። በምን ምክንያት እንደታሰርንና መታወቂያችን እንደተቀማ ንገሩን ብለው ሲጠይቋቸው ለፋኖ መረጃ እየተናገራችሁ ስለሆነና ከደጋማው አካባቢ የመጣችሁት ሁከት ለመፍጠር ነው የሚል መልስ ከከተማው ሰላምና ደህንነት እንድሁም ፖሊስ መምሪያው በኩል ተሰጥቷቸዋል። ግፍ በመርሳ ህዝብ ላይ በዚህ መልኩ ቀጥሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply