በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ከተማ ትናንት ከተደረገው የተሳካ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ሰልፉን አላስቀራችሁም የተባሉ አመራሮች እየታገዱ ነው፤ የከተማው ወጣቶችም እየታሰሩ ነው ሲሉ…

በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ከተማ ትናንት ከተደረገው የተሳካ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ሰልፉን አላስቀራችሁም የተባሉ አመራሮች እየታገዱ ነው፤ የከተማው ወጣቶችም እየታሰሩ ነው ሲሉ…

በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ከተማ ትናንት ከተደረገው የተሳካ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ሰልፉን አላስቀራችሁም የተባሉ አመራሮች እየታገዱ ነው፤ የከተማው ወጣቶችም እየታሰሩ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከራያ ቆቦ ነዋሪዎች ለማጣራት እንደሞከረው ትናንት ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በራያ ቆቦ ከተማ ከተካሄደው የተሳካ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ሰልፉን አላስቀራችሁም የተባሉ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ከስራ ታግደዋል። ከቆቦ ከተማ ወጣቶች መካከልም ኤርሚያስ ትኩዬ እና እስክንድር ሞላ የተባሉ ወጣቶች ዛሬ ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ማለዳ ላይ የታሰሩ ሲሆን አሁንም እንዲታሰሩ እየተፈለጉ ያሉ ወጣቶች ስለመኖራቸው ነው የደረሰን ምጃ ያመለከተው። ቤተሰብም ወደ ቆቦ እስር ቤት አቅንቶ ወጣቶችን ለማግኘትና ለመጠየቅ ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ለማወቅ ተችሏል። ብልፅግና መራሹ ስርዓት ዛሬም ከህወሀት ጎታችና ርዝራዥ አስተሳሰብ አለመላቀቁንና ወደለየለት አምባገነንነት በባሰ መልኩ መሸጋገሩን የነገሩን ነዋሪዎች ድርጊቱ የራያና የአካባቢውን ማህበረሰብ በተለይም ወጣቱን ክፉኛ ማስቆጣቱን አስታውቀዋል። መላው የአማራ ህዝብና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ይህን አምባገነናዊ አካሄድ አጥብቆ እንዲያወግዘውና እንዲታገለው ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል። በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቁም የሚለው ጥያቄ ከፓርቲ ጥያቄ በላይ የመላው አመራ ህዝብና የሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆች ሁሉ ጥያቄ ሊሆን ይገባዋል ነው ያሉት። ራያ ላይ የተደረገው ህዝባዊ ሰልፍ ፍፁም ሰላማዊ፣አማራዊ፣የተሳካና አርዓያነት ያለው በመሆኑ ሊመሰገን ሲገባ ወጣቶችን ማሰርና ማሳደዱ ተገቢ አይደለም፤ በመሆኑም በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል። ስለተፈፀመው እገዳና እየተፈፀመ ስላለው እስር መረጃ እንዲሰጡን በሚል ለራያ ቆቦ ከተማ ከንቲባ ለአቶ ተስፋዬ ማርዬ ብንደውልም የሚጠራ ስልካቸው ባለመነሳቱ ለጊዜው ሀሳባቸውን ለማካተት አልተቻለም። የአማራ ሚዲያ ማዕከል የራያ ቆቦ የፖሊስ አዛዥ ለሆኑት ለኮማንደር ታደሰ ደውሎ ለማነጋገር ያደረገው ጥረት መረጃ ለመስጠት ባለመፍቀዳቸው ስልካቸውን ዘግተዋል። በአንጻሩ የሰሜን ወሎ የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተመስገን በዞን ፖሊስ በኩል ከሰልፉ ጋር የተሰጠ የእስር ትዕዛዝም ሆነ አቅጣጫ የለም ሲሉ አስተባብለዋል። ራያ ቆቦ ላይ “የተከለከለ” ያሉት ሰልፍ መደረጉን አውስተው ከዛ ጋር ተያይዞ ስለተደረገው እገዳም ሆነ እስር የማውቀው ነገር የለኝም፤ እናጣራዋለን ብለዋል። የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወልደ ተንሳይን መኮንን በበኩላቸው እነማንና ስንት አመራሮች እንደታገዱ ባይገልፁም እገዳው ግን ቀደም ብሎ ከነበረው የህዝብ አስተያየትና ከስራ አፈጻጸም ግምገማ ጋር የተያያዘ እንጅ ሰልፉን በተመለከተ አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል። ጠብቆ መቆየቱ ለምን አስፈለገ? ትናንት የተቃውሞ ሰልፉ በተደረገ በማግስቱ ይህ እገዳ መደረጉ ከሰልፉ ጋር አይያያዝም ወይ? ለተባሉትም ሰው እንደዛ ሊያስብ ይችላል እንጅ እውነታው እሱ አይደለም ብለዋል። መንግስት የከለከለውን የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግም ትክክል ነው ብዬ አላምንም ያሉት አቶ ወልደ ተንሳይ ሀሳባቸውን ሳይጨርሱና ለጥያቄዎቸ ሙሉ ምላሽ ሳይሰጡ ስልካቸው ተቋርጧል። ተመልሰን በተደጋጋሚ ደውለን ለማነጋገር ብንሞክርም ጉዞ ላይ ስለሆንኩ ስልኩ ይቆራረጣል በማለት ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ሳይፈቅዱ ቀርተዋል። ዝርዝሩን በአማራ ሚዲያ ማዕከል የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply