በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ዋጃ፣ ጥሙጋ፣ አየር ማረፊያ እና አካባቢው ጥምር የወገን ጦር ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ ከአሸባሪው እና ወረሪው ትሕነግ አፈና ነጻ ወጥተዋል። አማራ ሚዲያ ማ…

በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ዋጃ፣ ጥሙጋ፣ አየር ማረፊያ እና አካባቢው ጥምር የወገን ጦር ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ ከአሸባሪው እና ወረሪው ትሕነግ አፈና ነጻ ወጥተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ ጥቅምት 7/2015 በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ዋጃ፣ ጥሙጋ፣አየር ማረፊያ እና አካባቢው ጥምር የወገን ጦር ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ ከአሸባሪው እና ወራሪው ትሕነግ አፈና ነጻ መውጣታቸውን የራያ ቆቦ ነዋሪዎች አስታውቀዋል። በኮረም እና አላማጣ በኩልም መልካም ዜና ስለመኖሩ እየሰማን ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ ከአላማጣ በኋላ 23 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ያለው ኮረምም ስለመያዙ ከአካባቢው ነዋሪዎች በስልክ እየሰማን ነው ብለዋል። በተለያዩ አቅጣጫዎች ጠንካራ የአጸፋ ምላሽ እና ከበባ የገጠመው እና በራያ አላማጣ በኩል ያለው የትሕነግ የሽብር ቡድን በከፍተኛ ሁኔታ ንብረት እየዘረፈ ሲጭን መዋሉ ተሰምቷል። ጥቅምት 7/2015 ዋጃ አሮጌው ገበያ፣ ጎታ ማርያም፣ አየር ማረፊያ እና አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ተጋድሎ ሲፈጸም መዋሉን ምንጮች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። ራያ ቆቦን ጨምሮ በከባድ የተናበበ ተጋድሎ ለድል የበቁት የዋጃ፣የጥሙጋ፣የአየር ማረፊያ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ስለመሆኑ የዐይን እማኞች ተናግረዋል። በራያ ባላ፣ ጨርጨር እና አካባቢውን ጨምሮ ሌሎች ነጻ ያልወጡ አካባቢዎች እንዳሉም ተገልጧል። በየአካባቢው ከሽብር ቡድኑ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየተባበሩ ያሉ ውስን ከፋፋይ የውስጥ ከሃዲዎችን በመለዬት ህጋዊ እና አስተማሪ እርምጃ መውሰድ ብሎም በጦርነት እየተገኘ ያለውን ድል በፖለቲካው ረገድ መድገም የክልሉ መንግስት አመራሮች ስራ በመሆኑ የትናንቱን ስህተት በማረም ቀድመው እንዲሰሩ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ከነዋሪዎች ቀርቧል። ተቆርጦ የቀረ የሽብር ቡድን ሊኖር ስለሚችል አካባቢውን ከመዘናጋት ይልቅ ሁሌም ነቅቶ እና ወትሮ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ እንደሚገባም መክረዋል። በተመሳሳይ በሰሜን ጎንደር ዞን ጥቅምት 3 እና 5/2015 አዳርቃይ እና ማይጠብሪ በከፍተኛ ተጋድሎ ነጻ መውጣታቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply