በሰሜን ወሎ ዞን በጋሸና ከተማ አስተዳደር በአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ጉዳት ከደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችና ከታላላቅ የሀይማኖት አባቶች ጋር የምክክር ውይይት ተካሄደ። ጥር04/…

በሰሜን ወሎ ዞን በጋሸና ከተማ አስተዳደር በአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ጉዳት ከደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችና ከታላላቅ የሀይማኖት አባቶች ጋር የምክክር ውይይት ተካሄደ። ጥር04/2014/አሻራ ሚዲያ/ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በጋሸና ከተማ አስተዳደር በወረራ በቆየባቸው አምስት ወራት ውስጥ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከባድ ሰብ አዊና ኢ ሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽም መቆየቱን የአካባቢው ማህበረሰብ ክፍሎች ተናግረዋል። እንደ አካባቢው ነዋሪዎች ገለጻ ሴቶች በጅምላ ተደፍረዋል፤እናት በልጆቿ ፊት ተደፍራለች፤ሚስት በባሏ ፊት ተደፍራለች፤የመንግስትና የግል ተቋማቶች ወድመዋል፤በተለይ እንደ ጤና ተቋማት ፣የትምህርት ተቋማት፣ባንኮች እንድሁም ሆቴሎች ሳይቀር የውድመቱ ሰለባ ሁነዋል ሲሉም ገልጸዋል። የሽብር ቡድኑ ህወሓት የጥፋት ጥጉን በተግባር አሳይቷል፤በአማራ ህዝብ ላይም ሂሳቡን በሚገባም አወራርዷል በማለት የገለጹ ሲሆን ወራሪውና ተስፋፊው ቡድን በእምነት ተቋማት ላይ አጸያፊ ቃላቶችን በመጻፍና ቅዱሳት መጽሐፍትና የቤተ እምነቱንም የመገልገያ መሳሪያዎችን ሳይቀር በከባድ መሳሪያ እንዳወደማቸውም ይናገራሉ። በውይይት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሰሜን ወሎ ዞን ሀገረ ስብከት ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ኤርሚያስ በከተማዋ ተገኝተው ለምዕመኑ አስተምህተ እግዚአብሔርን በመስበክ ጉዳት የደረሰባቸውን የከተማዋ ህዝቦች አጽናንተዋል።በጋሸና ከተማ አስተዳደርም ሲደርሱ በነዋሪው ማህበረሰብ ዘንድ ደማቅ አቀባበልም ተደርጎላቸዋል። እንደ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ኤርሚያስ ገለጻ አሸባሪው ቡድን በወልድያ ከተማ በወረራ በተሰማራበት ወቅትም ይህንኑ የሽብር ተግባሩን በከተማዋ ነዋሪዎች ሲተገብር የቆየ መሆኑንም አውስተው ይህ የጥፋት ተልዕኮ ይዞ የመጣ ቡድን ተመሳሳይ ጥፋቱን በጋሸና ከተማም ዳግም አሳይቷል ብለዋል። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ኤርሚያስም በሽብር ቡድኑ ተዘርፈው ከተወሰዱት የግለሰብም ይሁን የመንግስት ተቋማት እቃዎች የተረፉትን በአንዳንድ ግለሰቦች ዘንድ የሚገኙትን ለባለቤቱም ይሁን ለተቋማቱ እንድመልሱም አሳስበዋል። በመጨረሻም ብጹዕነታቸው አቡነ ኤርሚያስ ለከተማዋ ማህበረሰብ በከተማዋ ከእንግድህ ምንም አይነት የጭፈራም ሆነ የጫት ቤቶችን በመዝጋት ለቀጣይ ወጣቱም ይሁን ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ከመንግስት የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ስልጠና በመውሰድ ለሀገሩ ህልውና ሲል ራሱንም ሆነ ወገኑን ብሎም እናት ሀገሩን እንድያስከብርና ከባርነት ነጻም መሆን እንዳለበትና በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችንም በማሰብም ከጎናቸው እንድንቆምና ማገዝ ባለብን ልክም እንድናግዝ በተለይ ወላጅ ያጡ ህጻናትን ትኩረት አድርገን መስራት ይኖረብናል ብለዋል። የሽብር ቡድኑም ከዚህ እኩይ ተግባሩ እና ተልዕኮው እንድቆጠብም መልዕክት በማስተላለፍ ውይይቱን በጸሎት የመዝጊያ ስነ ስርአት አሳርገው ጥብቅ መልዕክትም አስተላልፈዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro ዘጋቢ ኤርሚያስ ጌታ ከጋሸና

Source: Link to the Post

Leave a Reply