
በሰሜን ወሎ ዞን ጃራ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች ደህንነታቸው አደጋ ላይ መውደቁን ገለጹ፤ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የአፋር ታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ 3 ሰዎች ስለመቁሰላቸው ተናግረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ወሎ ዞን ጃራ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች ደህንነታቸው አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል። ከሳምንት በፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ተገቢ ጥበቃ እየተደረገላቸው ባለመሆኑ የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ገልጸው ነበር። ጥር 30/2015 በአዋሳኝ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የአፋር ታጣቂዎች በጃራ መጠለያ ካምፕ ላይ በከፈቱት ተኩስ ከአካባቢው ነዋሪዎች 2፣ ከተፈናቃዮች 1 በድምሩ 3 ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጧል። የተመቱትም እግር እና እጃቸውን የቆሰሉ ስለመሆናቸው የተናገሩት ምንጮች የድሬ ሮቃ እና የጃራ ወጣቶች ባደረጉት ጥረት በተፈናቃዮች ብዙ ጉዳት አለመድረሱ ተገልጧል። ከጃራ በተኩሱ ምክንያት ዳግም የተፈናቀሉ በርካታ ወገኖችም በእግር ወደ ድሬ ሮቃ፣ ሀራ፣ ሀሮ እና ራያ ቆቦ እየሸሹ ስለመሆናቸው ተናግረዋል። በጃራ መጠለያ ካምፕ ከኦሮሚያ እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ በማንነታቸው የተፈናቀሉ ብዙ ሽህ ተፈናቃዮች ያሉ ሲሆን ስለተፈጠረው ነገር ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከውስጥ የደረሰው መልዕክት የሚከተለው ነው:_ “ኧረ የመንግስት ያለህ! እባካችሁ ለሚመለከተው አካል አድርሱልን አለምንም የመንግስት ጥበቃ በመጠለያ ጣቢያ አምቶ ከቶ ሊያስፈጀን ነው። ዛሬ በዋለው ተኩስ 3 ሰው ቆስሏል። መንግስት አምጥቶ በራብ መቅጣቱ አልበቃ ብሎት ከለላ ሳያደረግ ሜዳ ላይ ጥሎናል፤ እባካችሁ ለመላው ኢትዮጵያዊ እና ለመላው የዓለም ሕዝብ አሳውቁልን።” ፎቶ_ፋይል
Source: Link to the Post