
በሰሜን ወሎ ዞን ጃራ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ጥር 22/2015 ከረፋዱ 4 ሰዓት በሰሜን ወሎ ጃራ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል። ተፈናቃይ ወገኖች ባደረጉት ሰልፍ የተቃውሟቸው ዋነኛ ምክንያት:_ 1) ሰብአዊ እርዳታ በበቂ እየደረሰን አይደለም፣ 2) የደህንነት ዋስትና የለንም። የግል ታጣቂዎች በበጎ አድራጊነት በፈረቃ ይጠብቁናል። መደበኛ የሆነ የመንግስት የጸጥታ አካላት ለጥበቃ አልተመደቡም። በአካባቢው የጸጥታ ችግር አለ፤ በተለያዩ ጊዜያት የተኩስ ድምጽ የሚለየው አልሆነም፤ ለደህንነታችን እየሰጋን እንገኛለን። 3) ኦሮሚያን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ እና መፈናቀል እንዲቆም። 4) በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የፖለቲካ አመራሮች የጸጥታ አመራሮች ወደ አካባቢው ተመድቦ የሚሄደውን የመከላከያ ሰራዊት የተሳሳተ መረጃ እየሰጡ አማራውን ለተጨማሪ ጉዳት እየዳረጉት ስለሆነ መፍትሄ ይሰጠን። በመጠለያ ካምፕ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ የበመጠለያው ያለ የተፈናቃዩ ብዛት ከ15 ሽህ በላይ ይሆናል። በአብዛኛው ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ የሚበዙ ይሁን እንጅ ከቤንሻንጉል አካባቢም ተፈናቅለው የመጡ አሉ።
Source: Link to the Post