You are currently viewing በሰሜን ጎንደር ዞን ምስራቅ ጠለምት ወረዳ ከህወሓት አፈና ነጻ ያልወጡ የ3 ቀበሌ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ርሃብ እና ችግር የተጋለጡ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 12 ቀን…

በሰሜን ጎንደር ዞን ምስራቅ ጠለምት ወረዳ ከህወሓት አፈና ነጻ ያልወጡ የ3 ቀበሌ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ርሃብ እና ችግር የተጋለጡ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 12 ቀን…

በሰሜን ጎንደር ዞን ምስራቅ ጠለምት ወረዳ ከህወሓት አፈና ነጻ ያልወጡ የ3 ቀበሌ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ርሃብ እና ችግር የተጋለጡ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ጎንደር ዞን ምስራቅ ጠለምት ወረዳ በህወሓት አፈና እና ወረራ ስር የሚገኙ የ3 ቀበሌ እና የአንድ ጎጥ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ርሃብ እና ችግር የተጋለጡ ስለመሆኑ የመረጃ ምንጮች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ለትግራይ ተወላጆች ሲሰጥ በአፈና ስር ላሉ ለአማራ ተወላጆች ግን ምንም ዓይነት እርዳታ እየደረሰ እንዳልሆነ ተገልጧል። ከጥቅምት 2013 ጀምሮ በህወሓት ወረራ እና አፈና ስር የሚገኙ ነጻ ያልወጡ የአማራ ቀበሌዎችም:_ 1) ደገብራይ ቀበሌ፣ የደገብራይ ቀበሌ ከ10 ሽህ በላይ ህዝብ የሚኖርበት አካባቢ ሲሆን 8 አብያተ ክርስቲያናት እንዳሉበት ተጠቁሟል። 2) አምሾ ምድር ቀበሌ፣ በዚህ ቀበሌም 10 አብያተ ክርስቲያናት ያሉበት አካባቢ ነው። 3) ሜዳ ቀበሌ፣ 2 አብያተ ክርስቲያናት አሉበት፤ ከ5 ሽህ በላይ ህዝብ እንደሚኖርበት ተመላክቷል። ከእነዚህ ሶስት ቀበሌዎች በተጨማሪም በምስራቅ ጠለምት ወረዳ ጫጨሬ ቀበሌ ጥርሰጌ በተባለ ጎጥ የሚኖሩ አማራዎችም ነጻ አለመውጣታቸው ይታወቃል። በሰሜን ጎንደር 1) ምዕራብ ጠለምት፣ 2) ምስራቅ ጠለምት እና 3) ማይጠብሪ ከተማ አስተዳደር በዘር አጥፊው እና አሸባሪው ህወሓት የኃይል ወረራ እና አፈና ስር የነበሩ በትግል ነጻ የወጡ ወረዳዎች መሆናቸው ይታወቃል። ነጻ ያልወጡ ቀበሌዎች ነጻ እንዲወጡ እና አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ ይፈለግላቸው ዘንድ ጥሪ ተደርጓል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply