በሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ በምግብ ዕጥረት 25 ህፃናት መሞታቸው ተነገረ፡፡በሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ የጤና ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ሙሉቀን ትዛዙ ድርቁ ባስከተለው ጉዳት…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/tjSuQClJft22S_k4NxIm1OO8KhsQVGA9JbhFZ3yyobsp1dLlJ0t5ICTfqw9en7084qH24SaaCR3Ii4awnVo1DFRxVCAC088CNKZvyVCfc-Fu6WjzJfCTP3HNB6TOWa2N21FG_JZWvIxSvf7D5pkqjHK2Sa_rej1sbcad16rrEgx4Z9fDB_EQ9wmsy_arR7NbCRLJn8KJZNQsVl9vH_X0HvmWhJnhtdVrvquKi0PrMaZ_ESDNIu30NAWAW6w4KGJHBM7RmPNj6di-vQ8qXoLLWXVeNBkpGKjP21zY-Z7pj-VkwzV4HzHjmy1UGnhzici21d5izBWsGvgm49zh-1Z3Dg.jpg

በሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ በምግብ ዕጥረት 25 ህፃናት መሞታቸው ተነገረ፡፡

በሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ የጤና ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ሙሉቀን ትዛዙ ድርቁ ባስከተለው ጉዳት 2 ህፃናት እንዲሁም ተገቢውን ክብደት ሳያገኙ 23 ህፃናት ተወልደው መሞታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በድርቁ ከ2 መቶ 20 በላይ ህፃናት ከፍተኛ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው ገልፀዋል።

2 ሺህ 2 መቶ 27 ገደማ እናቶችም በከፍተኛ ርሃብ ውስጥ እንዳሉ የዞኑ የጤና ፅ/ቤትምክትል ሀላፊው ተናግረዋል ።

በዞኑ ከተላላፊ በሽታ ጋር ተያይዞ 1ሺህ 3 መቶ 96 ህፃናት በሳንባ ምች ተይዘዋል።

1ሺህ 4መቶ 56 ነዋሪ ለአጣዳፊ ተቅማጥ ተጋልጠዋል ፣ከዚሁም ውስጥ በግማሽ ከአምስት አመት በታች እንደሚገኙበትም ተገልጿል።

በወረዳው የሚደረገው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ምክንያት አሁንም የህፃናት ሞት መቀጠሉን የሚገልፁት ሀላፊው ድጋፍ እንዲደረግ አሳስበዋል።

በለአለም አሰፋ

ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply