በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ በግዳጅ ላይ ያለው ሀይል ሕወሓት ማይልሃም ላይ ሲቆፍርና ሲገነባቸው የነበሩ ምሽጎችን በመደምሰስ አካባቢውን ተቆጣጥሮ በድል እየገሰገሰ መሆኑ ተነገረ። አማ…

በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ በግዳጅ ላይ ያለው ሀይል ሕወሓት ማይልሃም ላይ ሲቆፍርና ሲገነባቸው የነበሩ ምሽጎችን በመደምሰስ አካባቢውን ተቆጣጥሮ በድል እየገሰገሰ መሆኑ ተነገረ። አማ…

በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ በግዳጅ ላይ ያለው ሀይል ሕወሓት ማይልሃም ላይ ሲቆፍርና ሲገነባቸው የነበሩ ምሽጎችን በመደምሰስ አካባቢውን ተቆጣጥሮ በድል እየገሰገሰ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከንጋቱ 12:20 ሰዓት ላይ በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ በማይልሃም በኩል በከሀዲው ሕወሓት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በአዳርቃይ ማይልሃም በኩል በሕወሓት ላይ በተወሰደው እርምጃ ማይልሃም ላይ ሴረኛው ቡድን በተራራ ላይ ሲቆፍራቸውና ሲገነባቸው የነበሩ ምሽጎችን በመደምሰስ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የቻለው የወገን ጦር ወደ ማይፀብሪ በድል እየገሰገሰ ነው ብለዋል ከአዳርቃይ ግንባር ያሉ ምንጮቻችን። በሴራ፣በሸፍጥና በፀረ አማራ ማኒፌስቶው የሚታወቀው ሕወሓት ከተከዜ ማዶ ተሻግሮ ለበርካታ ዓመታት በጉልበት ከያዛቸው የአማራ አፅመ እርስቶች እየተወሰደበት ያለውን ህግን የማስከበር እርምጃ ተከትሎ መቋቋም ባለመቻሉ ጥሎ እየፈረጠጠና እየተደመሰሰ ስለመሆኑም በተለያዩ ሚዲያዎች ተገልጧል። በጠለምት ደጃች ሜዳ በኩልም ከሁለት ቀናት በፊት ጀምሮ በሕወሓት ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉና የጠላት ጦር እየተፍረከረከ ነው፤ በወገን ጦር በኩል ደግሞ ድል እየተመዘገበ ነው ሲሉ ምንጮች ተናግረዋል። ሕወሓትና ተባባሪዎቹ ከፍተኛ ግፍና በደል ከፈፀሙባቸው በርካታ የአማራ አካባቢዎች መካከል ጠለምት፣አዳርቃይ፣ጃናሞራ፣በየዳና አካባቢው ተጠቃሾች ናቸው። በመጨረሻም የአማራ ህዝብና መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በአማራ ብሎም በሌሎች ወገኖች ላይ ተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመና እያስፈፀመ ብሎም በመከላከያ ሰራዊት ላይ አሰቃቂ የክህደት ጭፍጨፋ የፈፀመውን ሕወሓትን ከፈቀደ በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል አሻፈረኝ እስካለ ድረስ ግን ለመደምሰስ እየተወሰደ ያለውን እርምጃን በመደገፍ ረገድ እያደረጉት ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply