በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚና በአስተማሪነት ሙያ የሚያገለግለው መምህር መሰረት ጎበዜ ከላይ ታዘናል በሚሉ አካላት ያልተገባ ወከባ እና ማስፈራሪያ…

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚና በአስተማሪነት ሙያ የሚያገለግለው መምህር መሰረት ጎበዜ ከላይ ታዘናል በሚሉ አካላት ያልተገባ ወከባ እና ማስፈራሪያ…

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚና በአስተማሪነት ሙያ የሚያገለግለው መምህር መሰረት ጎበዜ ከላይ ታዘናል በሚሉ አካላት ያልተገባ ወከባ እና ማስፈራሪያ እየደረሰብኝ ነው ሲል ቅሬታ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ነዋሪ የሆነው መ/ር መሰረት ጎበዜ በአማራ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚነትና በደብር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በአስተማሪነት እንደተሰማራ ገልጧል። መምህር መሰረት ጎበዜ እንዳለው ከሰሞኑ “በአማራ ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ንጀል ይቁም!” በሚል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ እንደ አንድ አማራ ይመለከተኛል በሚል ሲያስተዋውቅ መሰንበቱን ተናግሯል። ይህን ያደረገው የአብን አባል በመሆኑ ነው በሚሉና ከዞን ታዘናል ባሉት በደባርቅ ወረዳ ት/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ከሌላ አንድ ሰው ጋር በመሆን ት/ቤት ድረስ በመምጣት እረፍ በማለት በቃል አስጠንቅቀውኝ ተመልሰዋል ነው ያለው። ጥቅምት 17 አቶ መላኩ እንዲሁም ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ደግሞ የወረዳው አፈ ጉባኤ የሆኑት አቶ ሰለሞን አንዳርጌ በማስተምርበት ደብር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በመምጣት አስጠንቅቀውኛል ብሏል። ተረጋግቸ እንዳላስተምር በ3 ቀናት ውስጥ ሁለት ጊዜ መጥተው ማስፈራሪያና ዛቻ መሰንዘራቸው እጅግ በጣም አሳዝኖኛል ሲል ነው መምህር መሰረት የተናገረው። እኔ ከማስተማር ሙያየ ባሻገር ሌላ ስራ እንደማልሰራ እያወቁ ለምን ማስፈራራትን እንደመረጡ አልገባኝም ያለው መ/ር መሰረት ይህ አካሄድ ለምንም ለማንም ስለማይጠቅም የሚመለከተው አካል እርምት እንዲሰጥበት ጠይቋል። በደባርቅ ከተማ የደብር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ተካ አስምሮ በበኩላቸው ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም የወረዳው ት/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ከሌላ አንድ ሰው ጋር በመሆን ት/ቤት ድረስ መጥተው ስለ መምህር መሰረት ተነጋግረናል ብለዋል። የአብን አባል ነው እንዲሁም ቅስቀሳ እያደረገ ነው በሚል ቅሬታ አንስተው እኛ የምናውቀው መ/ር መሰረት ስራውን ሲሰራ እንጅ ሌላ ነገር አናውቅበትም የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ጠቅሰው በዚህም ተግባብተው መመለሳቸውን አስታውቀዋል። ይህ ባለበት ሁኔታ ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም የወረዳው አፈ ጉባኤ አቶ ሰለሞን አንዳርጌ ከሌላ አንድ ሰው ጋር መጥተው የመ/ር መሰረትን ጉዳይ አጀንዳ ማድረጋቸውን የገለፁት አቶ ተካ ተነጋግረን ከተመለሱ በኋላ በድጋሜ ሌሎች መምጣታቸው አልገባኝም ብለዋል። ለወላጅ እና መምህራን ኮሚቴም ስለ መምህር መሰረት ሪፖርት አድርገው መሄዳቸውን እንደሰሙ የተናገሩት አቶ ተካ እኔም አካሄዱ ያልተገባ ተፅዕኖ የሚያሳድርና ለመምህራን የማይጠቅም በመሆኑ የሚመለከተው አካል እንዲያስተካክል ጠይቄያለሁ ብለዋል። የት/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ መላኩ ለተነሳባቸው ቅሬታ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀዱም። የወረዳውን አፈ ጉባኤ የአቶ ሰለሞን አንዳርጌን የስልክ አድራሻ ባለማግኘታችን ለጊዜው ምላሻቸውን ለማካተት አልተቻለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply