በሰሜን ጎንደር ጃን አሞራ ወረዳ በድርቅ በተባባሰው ረኀብ 32 ሰዎች እንደሞቱ ተገለጸ

https://gdb.voanews.com/01000000-0a00-0242-d5d2-08dbbf83f047_tv_w800_h450.jpg

በዐማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ሦስት ወረዳዎች፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እና የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት/USIDA/፣ ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ ርዳታ በማቋረጣቸው፣ በዞኑ 32 ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ፡፡

የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሓላፊ አቶ ይርዳው ሲሳይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ የርዳታው መቆምና በአካባቢው የተከሠተው ድርቅ ባስከተለው ረኀብ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ፣ ወደ 200ሺሕ የሚደርስ ሕዝብ፣ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያሻው ጠቁመዋል፡፡

አካባቢው ወትሮም ለድርቅ ተጋላጭ እንደኾነና ከ800ሺሕ ሕዝብ በላይ በርዳታ እንደሚኖር ያወሱት አቶ ይርዳው፣ ዓለም አቀፍ ለጋሾቹ ያቋረጡትን ሰብአዊ ርዳታ ዳግም እንዲጀምሩ አመልክተዋል፡፡ ረኀብ እንደጸናባቸው የተናገሩ፣ በዞኑ የጃንአሞራ ወረዳ የክልል ማርያም ቀበሌ ነዋሪዎችም፣ ሰብአዊነት የሚሰማው ዜጋ የርዳታ እጁን እንዲዘረጋላቸው ተማፅነዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply