
በሰበታ ወለቴ ቅዱስ ዮሃንስ ሰማዕትነት የተቀበለው ወጣት ዳዊት ክንፈ ይባላል። የመኖሪያ አካባቢውም ኮልፌ ሎሚ ሜዳ ሲሆን ቀብሩ በደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊሊጶስ መፈጸሙ ታውቋል። በቅዱስ ሲኖዶስ ህገ ወጥ የተባለው ቡድን የካቲት 3/2015 በወልቴ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በኦሮሞ የታጠቁ ኃይሎች ታጅቦ በገባበት ወቅት በልዩ ኃይል ተተኩሶበት በሰማዕትነት ማረፉ አይዘነጋም።
Source: Link to the Post