በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩ የጦር መኮንኖች ላይ አቃቢ ሕግ የሚያሰማው የምስክር ሂደት ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ እንደሚቀጥል ጠበቃ…

በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩ የጦር መኮንኖች ላይ አቃቢ ሕግ የሚያሰማው የምስክር ሂደት ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ እንደሚቀጥል ጠበቃ…

በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩ የጦር መኮንኖች ላይ አቃቢ ሕግ የሚያሰማው የምስክር ሂደት ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ እንደሚቀጥል ጠበቃ በሙሉ ታደሰ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩ የጦር መኮንኖች ላይ አቃቢ ሕግ የሚያሰማው የምስክር ሂደት ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ እንደሚቀጥል ጠበቃ በሙሉ ታደሰ ተናግረዋል። ጠበቃ በሙሉ እንደገለፁት ከመስከረም 27 ቀን 2013 እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት ድረስ አቃቢ ህግ 26 ምስክሮችን አሰምቷል። የምስክር ሂደቱም ከመደበኛ ሂደቱ ያልተለየ እና ይዘቱም ተመሳሳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።። የአቃቢ ህግ ምስክሮች ቃል መስጠትን ተከትሎም የተከሳሽ ጠበቆችና ጠቅላይ ፍቅላይ ፍ/ቤቱ መስቀለኛ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እውነታውን የማውጣጣት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠበቃ በሙሉ ገልፀዋል። አሁኑ ላይ ይሄ ምስክር እውነት፣ ያኛው ደግሞ ሀሰት መስክሯል ማለት አይቻልም ያሉት ጠበቃ በሙሉ ይህን ለመናገር የምስክር ሂደቱም ገና እየጀመረ በመሆኑና ስነ ስርዓቱም ስለማይፈቅድ ጭምር መነሻ አይኖረንም ሲሉ አክለዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በተከታታይ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን እንደሚሰማ ትዕዛዝ መስጠቱን የገለፁት ጠበቃ በሙሉ እስከዛው ጠበቆችና አቃቢ ህግ አጀንዳቸውን የሚያደራጁበት ጊዜ ይሆናል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply