You are currently viewing በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ የተከሰሱ የጦር መኮንኖች ከ70 ያላነሱ የመከላከያ ምስክር አሰምተዋል፤ ሂደቱ መጠናቀቁን ተከትሎ መዝገቡ ለብይን ተቀጥሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳ…

በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ የተከሰሱ የጦር መኮንኖች ከ70 ያላነሱ የመከላከያ ምስክር አሰምተዋል፤ ሂደቱ መጠናቀቁን ተከትሎ መዝገቡ ለብይን ተቀጥሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳ…

በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ የተከሰሱ የጦር መኮንኖች ከ70 ያላነሱ የመከላከያ ምስክር አሰምተዋል፤ ሂደቱ መጠናቀቁን ተከትሎ መዝገቡ ለብይን ተቀጥሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ የጦር መኮንኖች፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትና የአዴኃን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ከበደ ከ70 ያላነሱ የመከላከያ ምስክሮችን አሰምተዋል። ታህሳስ 11 ቀን 2014 የመከላከያ ምስክር አሰምተው መጨረሳቸውን ተከትሎም ታህሳስ 12 ቀን 2014 በነበረው ችሎት መዝገቡ ለብይን ተቀጥሯል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ነው ለጥር 30 ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው ተብሏል። በችሎቱ ከተከሳሾች ጋር ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ ተገኝተው እንደነበር ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply