በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ የተከሰሱት የጦር መኮንኖች የአቃቢ ህግ ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ለታህሳስ 27 ተቀጠሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ…

በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ የተከሰሱት የጦር መኮንኖች የአቃቢ ህግ ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ለታህሳስ 27 ተቀጠሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት አንድ ዓመት ከ5 ወራት በላይ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ባለስልጣናት ላይ በተፈፀመው ግድያ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የጦር መኮንኖች፣የአማራ ልዩ ሀይል አመራሮችና የአዴሃን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ከበደ ጉዳያቸውን በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እየተከታተሉ መሆኑ ይታወቃል። አቃቢ ህግ አሉኝ ካላቸው 165 ምስክሮች መካከል እስካሁን 65ቱን ያስመሰከረ ሲሆን ትናንት ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም በነበረው ችሎትም የቀድሞው የአማራ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው በአቃቢ ህግ ምስክርነት ቀርበው ቃላቸውን ሰጥተዋል ተብሏል። አቃቢ ህግ ከአቶ ላቀ አያሌው በተጨማሪ በተመሳሳይ ጉዳይ ይመሰክሩልኛል ያላቸውን ምስክሮች በቃኝ በሚል እንዳይመሰክሩ ያደረገ ሲሆን ከአሁን በኋላ 70 ምስክሮች ይቀሩኛል፣ ከመካከላቸውም የማላቀርባቸው ይኖራሉ ማለቱን ተከትሎ ችሎቱ ምስክሮችን ለይተህ አቅርብ በማለት ለታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply