በሰኔ 15ቱ ግድያ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ የልዩሀይል አመራር እና አባላት በግንባር ላይ ለነበሩ የክልሉ ልዩ ሀይል ድጋፍ አደረጉ። (አሻራ፣ጥር፣6/2013ዓ•ም ባህርዳር) በባህር…

በሰኔ 15ቱ ግድያ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ የልዩሀይል አመራር እና አባላት በግንባር ላይ ለነበሩ የክልሉ ልዩ ሀይል ድጋፍ አደረጉ። (አሻራ፣ጥር፣6/2013ዓ•ም ባህርዳር) በባህርዳር ሰባታሚት እስር ቤት በሴራ ታስረው የሚገኙት የአማራ ልዩ ሃይል አመራሮች እና አባላት ሌሎች እስረኞችን በማስተባበር ከዕለት ሬሽናቸው በመቀነስ (60)ስልሳ ኩንታል ስኳር እና (71)ሰባ አንድ ሺ ብር እና ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ሰራተኞች (25) ሃያ አምስት ሺ ብር ድጋፍ አድርገዋል። እርዳታውን በማስተባበር በታራሚዎች የተወከሉት የአማራ ልዩ ሀይል በላይ ዘለቀ ብርጌድ አዛዥ የነበሩት እና አሁን በእስር ላይ የሚገኙት ሻለቃ ሹመት የሱፍ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጋር በመሆን በባህርዳር የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ዋና መምሪያ ማዕከል ድጋፉቸውን አድርሰዋል። ሻለቃ ሹመት በንግግራቸው በግንባር ተገኝተን የትግሉ አካል ባንሆን እንኳን በቻልነው አጋርነታችንን ለመግለፅ እና የአማራ ልዩ ሃይል በመስዕዋቱ ያስመዘገበውን ድል ለማድነቅ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply