በሰንዳፋ በኬ ከተማ በ450 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ሆቴል፤በሰንዳፋ በኬ ከተማ የተገነባው ቱ አር ኤን ሰለሞን ሆቴል እና እስፓ የፊታችን ግንቦት 19 ቀን ሊመረቅ ነው ተብሏል፡፡በቀድሞው…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Pdmlqs3wC51wKq-whcb_VNOJ5owJNZ-G5doJan0uA88kLlTCyis8fTPqCsKG-owrVvMGPjn5WG_AaN-TeH1S4teUvTl4LIU2gb6VrXnd50YwKzmYNaD0jhSUKKCXcWevCrRxEsktGx9WWWtPJBJ01TfgcgeS6SBYKjup5kZOOoZLnZFiGulNh4RCksZBkc-KUyuIS76O8ReSADdyqoD8w1JicR8RE8FlInfekbpJGVO7PR3MNVa6OFvyCDHtJJJuNmxIMWCSrwCjxw8nacMC7aSmoMmINROu1DWxvjSYvHxSQhJgwjXDwwpaEagiXV6LfzCzo8qlw5LOZOeJ5_zQZQ.jpg

በሰንዳፋ በኬ ከተማ በ450 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ሆቴል፤

በሰንዳፋ በኬ ከተማ የተገነባው ቱ አር ኤን ሰለሞን ሆቴል እና እስፓ የፊታችን ግንቦት 19 ቀን ሊመረቅ ነው ተብሏል፡፡
በቀድሞው የደርግ መንግሥት ጦር ሠራዊት ውስጥ አገራቸውን በወታደርነት ባገለገሉት መቶ አለቃ ሰለሞን አዳሙ የተገነባው ይህ ሆቴል፣ ግንቦት 19 በደማቅ ስነ ስርአት እንደሚመረቅ ታውቋል፡፡

በ1983 ዓ.ም የደርግ መውደቅን ተከትሎ፣ የድለላ ሥራ መጀመራቸውን የሚናገሩት መቶ አለቃ ሰለሞን፤ በኋላም በ3ሺ ብር ካፒታል ወደ ንግድ ሥራ መግባታቸውን ያስታውሳሉ፡፡
ባለሃብቱ በከተማችን የሚታወቀው የቱ አር ኤን ሰለሞን ፈርኒቸር ባለቤት ሲሆኑ፤የሆቴሉ ህንጻ የእንጨት ሥራዎች በሙሉ የተከናወኑት በዚሁ ድርጅታቸው ነው ተብሏል፡፡

በሰንዳፋ በኬ ከተማ በ2ሺ ካ.ሜ ቦታ ላይ በግርማ ሞገስ የተንጣለለው ሆቴሉ፤ደረጃቸውን የጠበቁና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው 40 የመኝታ ክፍሎች አሉት፡፡
ከሬስቶራንት ባርና ካፌ በተጨማሪም የጃኩዚና ስፓ አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሏል፡፡

በተለይ የአካባቢው ቀዝቃዛ አየርና ያማረ ተፈጥሯዊ ዕይታ ሆቴሉን ተመራጭና ተወዳጅ እንደሚያደርገውም ተነግሯል፡፡
ሆቴሉ ያረፈበትን ቦታ በ2009 ዓ.ም መውሰዳቸውን የተናገሩት መቶ አለቃ ሰለሞን፤ የሊዝ ክፍያውን የፈጸሙት የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን መልቀቃቸውን ያስታወቁበት ዕለት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መቶ አለቃ ሰለሞን የአካባቢው ህዝብ ፍቅር ሆቴሉን በአካባቢው እንዲሰሩ እንዳደረጋቸውም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply