You are currently viewing በሰንዳፋ ወረዳ እግዚአብሔርአብ አካባቢ የዜጎች መኖሪያ ቤት በኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ መፍረሱ እንደቀጠለ መሆኑን ተጎጅዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 9 ቀን 201…

በሰንዳፋ ወረዳ እግዚአብሔርአብ አካባቢ የዜጎች መኖሪያ ቤት በኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ መፍረሱ እንደቀጠለ መሆኑን ተጎጅዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 9 ቀን 201…

በሰንዳፋ ወረዳ እግዚአብሔርአብ አካባቢ የዜጎች መኖሪያ ቤት በኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ መፍረሱ እንደቀጠለ መሆኑን ተጎጅዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ልዩ ዞን በአሁኑ አጠራር ሸገር ሲቲ ሰንዳፋ ወረዳ እግዚአብሔርአብ 49 ውሻሬ ሰፈር በብዛት አማራዎች የሚኖሩበት አካባቢ የካቲት 8/2015 ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እንዲፈርስ እየተደረገ ነው። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በመኪና እና በሰው ኃይል ከ400 በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ ተደርጓል። በብዛት አማራዎች ይኑሩበት እንጅ በአካባቢው የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የጉራጌ፣ የሀዲያ ተወላጆች እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ይኖሩበታል። የኦሮሞ ተወላጆች ቤት ተለይቶ አይፈርስም የሚሉት ነዋሪዎች አካሄዱ በጥላቻ በታወሩ ዘረኞች አሳፋሪ እና አሳዛኝ በሆነ መልኩ ብሬን በታጠቁ ታጣቂዎች ታጅቦ እየተፈጸመ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቀን ስራ ሰርተን ከገበሬዎች በመግዛት የገነባነው እና ቢያንስ ከአስር ዓመት በላይ የኖርንበት መኖሪያ ቤት አሁን አፍርሰውብን ጎዳና ላይ ወድቀናል ብለዋል ተጎጅዎቹ። ከተማ ላይ የሚከራይ ቤት ሲፈልጉም በእጅጉ ከመወደዱም በላይ እንዳታከራዩ ተብለናል የሚሉን እያጋጠመን ነው በማለት አስከፊነቱን ገልጸዋል። ቆርቆሮ ይዞ የተገኘ ባለንብረት በአፍራሾች ተቀምቶ ሊወሰድበት እንደሚችል ተገልጧል። ንብረት ጭነው ወደ ሌላ አካባቢ የሚሄዱ አማራዎች ከተገኙም በአፍራሽ ግብረ ኃይሉም ሆነ በሌሎች የኦሮሞ ታጣቂዎች ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚጠየቅ ተነግሯል። የቀንድ ከብቶችን ጭኜ ወደ ሌላ አካባቢ እንዳልሄድ የት ልትወስዳቸው ነው በሚል እስከ 20 ሽህ ብር ልጠየቅ በመሆኔ ግራ ገብቶኛል የሚሉት ሌላኛው ተጎጅ በማንነታችን እየተጠቃን በመሆኑ የአማራ ክልል መንግስት ካለ ወይም የሰብአዊነት ጉዳይ ያገባናል የሚል ሁሉ ይድረስልን ሲል ተማጽኗል። አማራ ለዘመናት ከሚኖርበት አካባቢው እና መኖሪያ ቤቱ ለምን ቤቱ ፈርሶ እንዲፈናቀል ይደረጋል? በሚል ለመስተዳድር አካላት ስንጠይቅም “በሰላም ለቃችሁ ብትሄዱ ይሻላል” በማለት ይመልሱናል ያሉት ተጎጅዎች ከፍተኛ ጥላቻ እንዳላቸው ተመልክተናል ብለዋል። ከወለደች 8 ቀን የሆናት እናትንም ቤት በማፍረስ አባረዋል፤ ተማሪዎች ወደ ት/ቤት እንዳይሄዱ ተደርጓል ሲሉም አስከፊነቱን አክለው ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply