በሱዳኑ ጦርነት የካርቱም ህንጻዎች እየጋዩ ነው

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-a260-08dbb77a5cb4_w800_h450.jpg

ስድስተኛ ወሩን በያዘው ውጊያ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ካርቱም በሚገኘው የጦር ኃይሉ ዋና መ/ቤት ላይ በከፈቱት ጥቃት ዛሬ እሁድ የእሳት ቃጠሎ መታየቱን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

“ዛሬም ውጊያው በሱዳን ጦር ኃይሎች ዋና መምሪያ ዙሪያ በተለያዩ የጦር መሣሪያዎች እየተካሄደ መሆኑን” እማኞች ከሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ለኤ.ኤፍ.ፒ ተናግረዋል፡፡

ከካርቱም 350 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው ኢል ኦቤይድ ከተማም ሌላ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ተዘግቧል፡፡

በአገሪቱ ጦር ኃይሎችና ፈጥኖ ደራሹ ጦር መካከል ትናንት ቅዳሜ ካርቱም ውስጥ ሲካሄድ በዋለው ውጊያ በርካታ ህንጻዎች መጋየታቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

በካርቱም ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው መንደሮች የሚካሄደውን የማያቋርጥ የአየር ድብደባ፣ የመድፍ ተኩስ እና የጎዳና ላይ ጦርነት የሸሹ 2.8 ሚሊዮን ሰዎችን ጨምሮ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተመልክቷል።

ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ሚያዝያ ወር አንስቶ እስካሁን 7ሺ500 ሰዎች መሞታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply