በሱዳን ምዕራባዊ ዳርፉር በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ የ32 ሰዎች ህይወት አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራባዊ ዳርፉር…

በሱዳን ምዕራባዊ ዳርፉር በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ የ32 ሰዎች ህይወት አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራባዊ ዳርፉር አረብ ነን እና አረብ አይደለንም በሚሉ ቡድኖች መካከል ግጭቱ ተቀስቅሷል። የሱዳን መንግስት ግጭቱን ተከትሎ በግዛቱ እንቅስቃሴ የሚገድብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አውጇል። በዳርፉር ግዛት መዲና ጂኒና ዋና ሆስፒታል የቀድሞ ሜዲካል ዳይሬክተር ሳላህ ሳሊህ ከሟቾቹ 32 ሰዎች በተጨማሪ በግጭቱ ክፉኛ የቆሰሉ ቢያንስ 79 ሰዎች ህክምና በመሻት ሆስፒታል መምጣታቸውን ገልፀዋል። ወደ ሆስፒታል ያልመጡ ተጎጂዎች በመኖራቸው ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ገልፀዋል። ግጭቱ ሊቀሰቀስ የቻለው በጂኒና ከተማ በትላንትናው እለት አንድ ከአረብ ጎሳ የሆነ ግለሰብ በገበያ ስፍራ መገደሉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ አረብ አይደለንም በሚሉ የጎሳ አባላት ላይ የአፀፋ የበቀል ጭፍጨፋ በመፈፀማቸው ነው። በካርቱም የሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቢ ህግ የሚመራ ልዑክ ወደ ስፍራው በመላክ ሁኔታው እንዲረግብ ይሰራል ሲል ይፋ አድርጓል። ከአንድ አመት በፊት በተመሳሳይ አረብ አይደለንም እና አረብ ነን በሚሉ ጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 54 ሰዎች ሲገደሉ ከ40ሺ በላይ ሰዎች ለስደት ተዳርገዋል።አብዛኞቹም ወደ ጎረቤት ሀገር ቻድ ተሰደዋል። ይህ ግጭት የተሰማው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል በዳርፉር ያለው ተልዕኮ ማብቃቱ የፀጥታው ምክር ቤት ካሳወቀ ከሁለት ሳምንታት በኃላ ነው። ምንጭ_ኢትዮ 360

Source: Link to the Post

Leave a Reply