በሱዳን በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት 48 ሰዎች ተገደሉ፡፡ (አሻራ ጥር 9፣ 2013 ዓ.ም) ለ13 ዓመታት ያህል በተባበሩት  መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል የነበረው የዳርፉር ግዛት  ወደ ብጥ…

በሱዳን በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት 48 ሰዎች ተገደሉ፡፡ (አሻራ ጥር 9፣ 2013 ዓ.ም) ለ13 ዓመታት ያህል በተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል የነበረው የዳርፉር ግዛት ወደ ብጥ…

በሱዳን በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት 48 ሰዎች ተገደሉ፡፡ (አሻራ ጥር 9፣ 2013 ዓ.ም) ለ13 ዓመታት ያህል በተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል የነበረው የዳርፉር ግዛት ወደ ብጥብጥ ተመልሷል፡፡… በብጥብጡም ቅዳሜ ምሽት ብቻ 48 ሰዎች እንደተገደሉ አልጀዚራ ከስፍራው ዘግቧል፡፡ የሱዳን የባለሙያዎች ማህበር ለስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን፣ የተጎዱት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረገ ነው፡፡ ዳርፉር አፍሪካዊ ነኝ እንጂ አረባዊ አይደለሁም የሚል የጎሳ ቅኝት አላቸው፡፡ ካርቱም መሩ መንግስት ደግሞ በአረባዊ ጎሳ ነኝ ብሎ ያስባል፡፡ ደቡብ አፍሪካ አረባዊ አይደለሁም ብላ ራሷን ከ10 ዓመት በፊት ሀገር አድርጋለች፡፡ 7 ሚሊየን ህዝብ የሚኖርባት ዳርፉር የነፃ አውጪ ንቅናቄ ያለባት ግዛት ስትሆን፣ ከ13 ዓመት በፊት፣ 300 ሺ ንፁሃን በአልበሽር እንደተጨፈጨፉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡ ይህም አልበሽርን የጦር ወንጀለኛነት ክስ አሰነስቶበታል፡፡ ያልሰከነው አዲሱ የሱዳን አስተዳድር ደግሞ የሱዳንን አንድነት አስጠብቄያለሁ ብሎ የተባበሩት መንግስታት ሀይል እንዲወጣ ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ሀይልም እየወጣ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ብቻ 829 ወታደሮች በዳርፉር ያሏት ሲሆን፣ ሁሉም በመውጣት ሂደት ላይ ናቸው፡፡ የሱዳን የሽግግር መንግስት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጥሶ መግባቱን እና መሬቱን መውረሩን እንደ ድል ለሀገሩ ዜጎች ቢናገርም የሱዳን አንድነት አልመጣም፡፡ በትናንትናው ዕለት የሱዳን ወታደራዊ ገዥው አርቡሃን ” የሱዳን ጦር ግዛታችን እንድንቆጣጠር የፈቀደሉን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ናቸው፡፡ ራሳቸው በፈቀዱት ተመልሰው ሱዳን የሶስተኛ ወገንን ከሳሽ ማድረጋቸው ጤነኝነታቸውን እንድጠራጠር አድርጎኛል” ሲሉ በአልጀዚራ አረበኛ ተደምጠዋል፡፡ “ሶስተኛ ወገን ” ግብፅን ማለት ሲሆን አልቡርሃን በአደባባይ የግብፅ ጠበቃ ሆነው ቆመዋል፡፡ በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሱዳን ወታደር ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲገባ ለምን? እንዴት? እንደፈቀዱ ግልፅ ማብራሪያ አልተሰጠም ፡፡ ኢትዮጵያ ጉዳዮን ውሸት ነው? ወይም እውነት ነው? የሚል መረጃ እስካሁን አልሰጠችም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ካልነካ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኃላ አይሉም የሚል ወቀሳ እየተነሳባቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የውጭ ሀይሎች የኢትዮጵያን አንድነት ለመበጣጠስ የሚሰሩት ሴራ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገር ሉዓላዊነት አይደራደሩም የሚሉም አልጠፉም፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዮ ላይ ግልፅ ማብራሪያ አለመስጠቱ የውዝግብ ምንጭ ሆኗል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply