በሱዳን በኩል “መሬቱን ውሰዱ ተብልናል የሚለው ሀሳብ ትክክል አይደለም፤ አሁንም አቋማችን የሱዳን ጦር ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ እንነጋራለን” ያሉት ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ዲና…

በሱዳን በኩል “መሬቱን ውሰዱ ተብልናል የሚለው ሀሳብ ትክክል አይደለም፤ አሁንም አቋማችን የሱዳን ጦር ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ እንነጋራለን” ያሉት ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ዲና…

በሱዳን በኩል “መሬቱን ውሰዱ ተብልናል የሚለው ሀሳብ ትክክል አይደለም፤ አሁንም አቋማችን የሱዳን ጦር ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ እንነጋራለን” ያሉት ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሰሞኑን የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሌተናል ጀነራል አልቡርሃን የተናገሩትንም ትክክል አይደለም ብለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ “አጥፊ ሐይሎች የእናተን ድንብር ተጠቅመው ወደ እኛ እንዳይገቡ ማለት እናንተ ግቡ ማለት አይደለም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ለሱዳን መሪዎች እኛ ወደ ሰሜን ህግ የማስከበር ስራ ላይ በመሆናችን የእናተን መግቢያ ድንበሮች ጠብቁ ስለማለታቸው ነው አምባሳደሩ የጠቀሱት። ሱዳንን ለማረጋጋት ኢትዮጵያ በርካታ ስራዎችን ስለመስራቷና በሁለቱ ሀገራት የከፋ የነቆራ ታሪክ አለመኖሩን ያወሱት አምባሳደሩ በሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው፤ መሬቱን ውሰዱ ተብልናል የሚለው ሀሳብም ትክክል አይደለም፣ አሁንም አቋማችን የሱዳን ጦር ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ እንነጋራለን ስለማለታቸው በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ተዘግቧል። አምባሳደሩ በቀደመውም ይሁን በዛሬ መግለጫቸው የሱዳን ጦር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የተወሱኑ አካላት ፍላጎት እንደሆነ ቢገልፁም በተለያዩ ጊዜያት ባለሀብትና አርሶ አደሮችን እያፈናቀሉ፣ እየዘረፉና የሀገርን ድንበር ጥሰው እየተስፋፉ ያሉ አካላት ግን ከመንግስት እዝ እየተቀበሉ ወረራ እየፈፀሙ መሆኑ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply