በሱዳን የሚገኘው ኤል ፋሽር የምድር ሲኦል ሆኗል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከተጠየቀዉ ገንዘብም 12 በመቶዉን ብቻ ማግኘቱንም ገልፃል። የተባ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/H-EaYesA__C_wWNazBq7ebYbTGYWzTjsWLu8gzQLSBQSmSpZ1kPVy18Gpegk4Q6q3X1KtmkEnc26bnHsGNSzG2ceGTXDOJFWCtAYiJVdu_ZiYrwXybW4Ft0osbqK2JoxT7iNJICQmhmPp6MZQASZqrYgW2gnqXsazUl9Awa-QGSbQyDNrwtDebNcBy0Vrs51BAssJF6eoNgyEGckgVvxjBlRqo2pF-WMOMv1jt3xz_siixw7Y_PaT32HLItV_bU4sqm8vEkSiyQzXlytXUuJraukFrGlEezCYuC9GTxb9lBQ7_nUm_19CQ5GBeIzfR5oDViFnPlRcGTbRJrL4Q_cFw.jpg

በሱዳን የሚገኘው ኤል ፋሽር የምድር ሲኦል ሆኗል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከተጠየቀዉ ገንዘብም 12 በመቶዉን ብቻ ማግኘቱንም ገልፃል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ሃላፊ በሱዳን ዳርፉር ግዛት እየተባባሰ የመጣዉን ግጭት በተመለከተ አስተያየታቸዉን የሰጡት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ባለስልጣን በመሬት ላይ ያለዉ ሁኔታ “የምድር ሲኦል” ሲሉ ገልፀዉታል።

በምዕራብ ዳርፉር ግዛት የሱዳን ጦር ሃይሎች የመጨረሻ ምሽግ የሆነችዉ ከተማ አቅራቢያ የሚካሄደዉ ጦርነት ወደ ሁለገብ ጦርነት ሊቀየር ይችላል በሚል ስጋት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በኤል ፋሸር እየተጠሉሉ ነዉ ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ቢሮ ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ቢያንስ 58 ሰዎች በኤል ፋሸር አካባቢ መገደላቸዉን ገልፃል።

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 10 ቀን 2016 ዐ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply