በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ

በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በሱዳን የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን የገዳሪፍ ግዛት የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ አልሀፊዝ መሃመድ እንዲሁም በገዳሪፍ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ተወካይ አንድሪው ኤምቢጎሪ ጋር በሱዳን የሚገኙ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚህም በትግራይ ክልል ህግ የማስከበር ዘመቻ በመጠናቀቁ ዜጎች ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ በተመለከተ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ እንዲሁም ሁለቱ አካላት መመለስ የሚፈለጉ ስደተኞችን በተቻለ ፍጥነት በመለየት ወደ ተግባር ይገቡ ዘንድ ጥያቄ አቅርበዋል።

ተወካዮቹም በበኩላቸው ስደተኞችን በማነጋገር ፍቃደኛ የሆኑትን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ከሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

The post በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply