በሱዳን ዳርፉር  18 ሰዎች ተገደሉ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 20፣ 2013ዓ.ም) በሱዳን ዳርፉር የተነሳው ብጥብጥ ዛሬም አልሰከነም፡፡  ትናንትና  15 ንፅሃን የተገደሉ ሲሆን፣ ዛሬ ሁለት ተገለዋ…

በሱዳን ዳርፉር 18 ሰዎች ተገደሉ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 20፣ 2013ዓ.ም) በሱዳን ዳርፉር የተነሳው ብጥብጥ ዛሬም አልሰከነም፡፡ ትናንትና 15 ንፅሃን የተገደሉ ሲሆን፣ ዛሬ ሁለት ተገለዋ…

በሱዳን ዳርፉር 18 ሰዎች ተገደሉ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 20፣ 2013ዓ.ም) በሱዳን ዳርፉር የተነሳው ብጥብጥ ዛሬም አልሰከነም፡፡ ትናንትና 15 ንፅሃን የተገደሉ ሲሆን፣ ዛሬ ሁለት ተገለዋል፡፡… እንደ ቢቢሲ ዘገባ፣ የብጥብጡ ምንጭ የአፍሪካ እና የተባበሩት መንግስታት ከዳርፉር መውጣት የለበትም እና አለበት በሚለው የተነሳ ውዝግብ ነው፡፡ ዳርፉር እስካሁን በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሀይል የሚመራ ሲሆን፣ የሱዳን የሽግግር መንግስት ራሴን በራሴ እመራለሁ በማለቱ የፀጥታ አካሉ ለመውጣት ዳር ደርሶ ነበር፡፡ የሱዳን የሽግግር መንግስት በዳርፉር እና በብሉናይል ግዛት ካሉ አማፂያን ጋር ከሁለት ወር በፊት የተኩስ አቁሞ ስምምነት በጁባ -ደቡብ ሱዳን አድርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን በሱዳን ያም ሆኖ ለውጥ ሳይመጣ ቀርቶ እስከዛሬ ብቻ 18 ሰዎች በታጣቂዎች ተገለዋል፡፡ ቀጠናው እንዲረጋጋ ኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሀይል በዳርፉር እና በአብዮ ግዛቶች ኢትዮጵያ የመከላከያ ሀይሏን አሰማርታ ነበር፡፡ ሱዳን ግን የኢትዮጵያን ውለታ ዘንግታ ከግብፅ ጎን ቁማ ኢትዮጵያ በውስጣዊ ችግሯ ስትገባ ኢትዮጵያን ወራለች፡፡ በወረራውም የአንድ ቢሊየን ብር ንብረት አውዳማለች፡፡ ልዮ ወታደራዊ ሜካናይዝድም አሰማርታለች ፡፡ ኢትዮጵያን በመውረር የውስጥ አንድነቷን ለመጠገን ብትሻም ሳይሳካላት ቀርቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም ሱዳን የኢትዮጵያን ግዛት ለቃ ካልወጣች አፀፋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ ፅንፈኛ የፖለቲካ ልሂቃን የሱዳን መውረር እያበረታቱ ሰንብተዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply