በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከ 3 ሚልዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ ረሀብ አደጋ ተጋለጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በዘንድሮ…

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከ 3 ሚልዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ ረሀብ አደጋ ተጋለጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በዘንድሮው ዓመት የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው አደጋ በክልሉ 17 ወረዳዎች የግብርና ምርት ሙሉ በሙሉ ውጤት አልባ መሆናቸውን ተከትሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ለከፍተኛ ረሀብ ተጋልጧል። ይሁን እንጂ እስከአሁን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃውን ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም ለፌደራል መንግሥት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑና አስፈላጊ ትኩረትና ድጋፍ ማግኘት ባለመቻሉ ህዝቡ የመኖር እና ያለመኖር ፈተና እንደተጋረጠበት ለአሚኮ አሳውቋል። የሲዳማ ህዝብ ለብዙ ዘመናት የምግብ ዋስትናውን ያለ ማንም እርዳት ያረጋገጠ፣ ከእራሱ አልፎ ሌላውን የሚመግብ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም እራሱን በእራሱ የማስተዳደር የፖለቲካ ጥያቄው በተመለሰ ማግስት ትኩረት ያላገኘ የረሀብ አደጋ፣ የህዝብን ፍላጎት ያማከለ ልማት እጦት፣ የመልካም አስተዳደር ችግር እየተፈታተነው ይገኛል። ለዚህም ማሳያዎች ሰሞኑን የክልሉ ኦዲት ቢሮ ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሠረት በአንድ አመት ውስጥ 197,025,436.32 ብር ጉድለት ተገኝቷል። ከዚህም ባሻገር የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በዞን መዋቅር ወቅት የነበረ እና የአንድ አመት የክልሉ ፋይናንሻል ሪፖርት መረጃ በማሸሽ ተጠያቂነት እንዳይኖር ማድረጉ ይታወሳል። የሆነ ሆኖ የክልሉ መንግስት ለተከሰተው ረሀብ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መረጃውን ለፌደራል መንግሥት፣ ለብሔራዊ አደጋ እና ስጋት፣ ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንዲሁም ለተራድኦ ድርጅቶች እንዲሁም ለሚመለከታቸው ሁሉ እንዲያሳውቅና አስቸኳይ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ የአደጋው ተጋላጮች ገልፀዋል። ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው እየጠየቅን እንደየአስፈላጊነቱ በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ ይዘን እንቀርባለን። የሲዳማ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply