በሲዳማ ክልል በተፈጸመው የአፈር ማዳበሪያ ስርቆት ላይ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ተሳታፊ እንደነበሩ ተገለጸ፡፡

በሲዳማ ክልል በ16 ወረዳዎች እንዲሰራጭ ተብሎ በቀረበው የአፈር ማዳበሪያ ስርቆት ላይ፣ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ተሳታፊ መሆናቸውን የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨማሮ በወንጀሉ ላይ ተሳታፊ የነበሩ 148 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

የተሰረቀው የአፈር ማደበሪያ 25 ሺህ ኩንታል ነው ያሉት ሃላፊው በብር ሲተመን 38 ሚሊየን ብር እንደሚደርስ ገልጸለዋል፡፡

አቶ አለማየሁ ጤሞቲዎስ አክለውም የአፈር ማዳበሪያው ወደ አርሶ አደሮች ቢደርስ ኖሮ 4 መቶ 42 ሺህ ኩንታል ምርት ያስገኝ ነበር ብለዋል፡፡

መንግስት የእረሶ አደሩን ህይወት ለማሻሻል በድጎማ የሚያመጣውን የአፈር ማዳበሪያ አረሶ አደሩን እንዲያገልግል የተቀመጠው ባለሞያ ከነጋዴዎች ጋር ተመሳጥሮ ለራሱ ጥቅም ሲያውለው መቆየቱን ቢሮ ደርሶበታል ነው ያሉት ፡፡

በመንግስት ሃላፊነታቸው ከቀበሌ አንስቶ እስከ ክልል አመራርነት ድረስ የነበሩ 148 ሰዎች ከሃላፊነታቸው ተነስተው ጉዳያቸው በህግ እየተጣራ እንደሚገኝ የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ጥቅምት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply