በሲዳማ ክልል 80 በመቶ የትራፊክ አደጋ የሚደርሰው በሞተር ሳይክሎች መሆኑ ተነረ፡፡በክልሉ 80 በመቶ የትራፊክ አደጋ የሚደርሰው በሞተር ሳይክሎች እንደሆነ የነገረ ሲሆን እነዚህ ተሽከርካሪዎ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/umQt0eEHji-3QnFCRckDDrbfgq33zceZ1Nc4_HXshC1-DzjXPQkpb3CjvPSh0MMDAvSlCq2bbvjbZReeelsfXmqqcYn_js2fJU78lLcJ5obN27tdQwmp8vm--gPhG6fkXhb9WW1MWCtAtAVid_STdnyC1oqJk4MQzmIor4yuB0K3vDjpdyhuJdijdXD0UBWC123IyznweL4EPwQYwYi7iCDxRBt9Hfsga1Ryz34FKZ44HeXsZ1iRC4QAnhfZlZkrmN0BPSdptKL_KaobbjjSYXZGEH4yFoFPnyqlQE2uBtHbzweBD9oYB_VetebRKlQt54e_QC_RnSb4TgVhJ1rHLg.jpg

በሲዳማ ክልል 80 በመቶ የትራፊክ አደጋ የሚደርሰው በሞተር ሳይክሎች መሆኑ ተነረ፡፡

በክልሉ 80 በመቶ የትራፊክ አደጋ የሚደርሰው በሞተር ሳይክሎች እንደሆነ የነገረ ሲሆን እነዚህ ተሽከርካሪዎች ወደ ትላልቅ ከተሞች እንዳይገቡ እገዳ መጣሉ ጣበያችን ሰምቷል፡፡

የሲዳማ ክልል መንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኋላፊ አቶ ታምሩ ታፌ በክልሉ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የተጠናከረ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረው በየጊዜው ለማህበረሰቡም በቂ ግንዛቤ እየተፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡

በክልሉ በበጀት አመቱ ስምንት ወራት 113 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን እንዳጡ የገለጹት አቶ ተምሩ በ2015 በጀት አመት ከደረሰው የትራፊክ አደጋ ጋር ሲነጻጸር አሁን ላይ 48 በመቶ የቀነሰ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥሩ የበለጠ ለማጠናከር የአልኮል ቴስተር እና የራዳር ድጋፍ እንዲገኝ ክልሉ ለትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴርን መጠየቁ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በክልሉ አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች በግንባታ ሂደት ውስጥ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ታምሩ፤ ለነባር 33 መንገዶች ጥገና መደረጉን አብራርተዋል።

ሔኖክ ወ/ገበርኤል

ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply