በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ የወሎ አማራዎች በጋራ በመሆን ለዘመቻ ሕልውና ያሰባሰቡትን የገንዘብ ድጋፍ ገቢ ማድረጋቸውን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም…

በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ የወሎ አማራዎች በጋራ በመሆን ለዘመቻ ሕልውና ያሰባሰቡትን የገንዘብ ድጋፍ ገቢ ማድረጋቸውን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር ከሳውዲ አረቢያ የቀጥታ የስልክ ውይይት ያደረጉት በቀድሞው ወሎ ክፍለ ሀገር በአቀፍታ ወረዳ 031 ቀበሌ የተወለዱት አቶ ኡመር አህመድ አሊ ይባላሉ። ከኢትዮጵያ ከወጡ ከ20 በላይ ዓመታትን አስቆጥረዋል። ላለፉት በርካታ ዓመታት የዘር ፍጅት ሲፈፅም የኖረው አሸባሪው የወያኔ ቡድን በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በአማራ እና በአፋር አካባቢ ከሰሞኑ እየፈፀመው ስላለው የለየለት ወረራ እና ጭፍጨፋን በተመለከተ የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል። በተለይም በማይካድራ፣በቆቦ አጋምሳ እና በአፋር ተፈናቃዮች ላይ የፈፀመውና በግልፅ የተነገረንን ፍጅት የጠቀሱት አቶ ኡመር ትሕነግ ለኢትዮጵያ የማይጠቅም ነቀርሳ ድርጅት ነው ብለውታል። በመሆኑም የአማራ ክልል መንግስት የጠራውን የክተት አዋጅ እና ዘመቻ ሕልውናን ለማስከበር በሚደረገው ጥረት የድርሻችን ማበርከት አለብን በሚል በሳውዲ አረቢያ የምንገኝ የደቡብ ወሎ ልጆች በጋራ በመሆን ገንዘብ በማሰባሰብ ለደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ገቢ አድርገናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ገቢ የተደረገበት የአካውንት ቁጥርም 1000408164145 መሆኑ ተገልጧል። “ከገንዘብ ድጋፍ አልፈን እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ ለመክፈል ዝግጁ ነን” ያሉት የድጋፍ አስተባባሪው አቶ ኡመር ለጊዜው ከ310 ሽህ ብር በላይ ገቢ አድርገናል ብለዋል። ድጋፉም በግዳጅ ቀጠና ሆነው አሸባሪውን የትሕነግ ዘር አጥፊው ቡድንን እየደመሰሱ ለሚገኙ ለአማራ ልዩ ኃይል፣ለፋኖ፣ለሚሊሻና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት መሆኑ ተጠቅሷል። ተፈናቃዮችን በመደገፍ ረገድም የሁሉም አካላት እርብርብ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ከመንግስት ጎን በመሆን የድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ አስታውቀዋል። በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ መላው አማራና ሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በጋራ በመሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪውን ትሕነግ በተባበረ ክንድ በመደምሰስ የሀገራችን ነጻነትና ክብር እንደ ቀደምት ጀግኖቻችን እናስከብር ሲሉ ጥሪ አድርገዋል። የትግራይ ህዝብን ከኢትዮጵያ ለመነጠል አስቦ እየሰራ ያለውን የሽብር ቡድን ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር በመቆም አጥብቆ መቃወምና መታገል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply