You are currently viewing በሳውዲ አረቢያ ጅዳ በእስር ላይ የሚገኙ የጤና መታወክ ያለባቸው ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት የሚደረገው ጉዞ በዘገዬ ቁጥር የሚፈጸምብን ግፍ እየጨመረ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉ…

በሳውዲ አረቢያ ጅዳ በእስር ላይ የሚገኙ የጤና መታወክ ያለባቸው ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት የሚደረገው ጉዞ በዘገዬ ቁጥር የሚፈጸምብን ግፍ እየጨመረ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉ…

በሳውዲ አረቢያ ጅዳ በእስር ላይ የሚገኙ የጤና መታወክ ያለባቸው ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት የሚደረገው ጉዞ በዘገዬ ቁጥር የሚፈጸምብን ግፍ እየጨመረ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሳውዲ አረቢያ ጅዳ የጤና መታወክ ያለባቸው በሚል የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ቅድሚያ ወደ ሀገር ቤት ይመለሳሉ ቢባልም ባላወቅነው ምክንያት በእኛ ላይ ሂደቱ ተቋርጦብናል ሲሉ እስረኞች ተናግረዋል። ተለይቶ ያደረ ህመም ያላቸውና የህክምና ክትትል ስለሚያስፈልጋቸው ከሁሉም ቀድመው ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ በሚል ለብቻ ከተለዩት ከ100 በላይ ከሚሆኑ የግፍ እስረኞች መካከል 50 የሚሆኑት ብቻ ከአንድ ወር በፊት ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል ይላሉ። ይሁን እንጅ ከ50 በላይ የሚሆኑት እስካሁን በከፋ የጤና ችግር ላይ መሆናቸውንና በቂ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ገልጸው ኢምባሲውም መጥቶ እየጎበኘን አይደለም ብለዋል። ሴት፣ህጻን ልጅ እና የህክምና ክትትል ያላቸው እንደአብነት ካንሰር፣ቲቪ፣ የደም ግፊትና ሌሎች ታካሚዎች በቅድሚያ ወደሀገር ቤት ይጓዛሉ ተብሎ እንደነበር ተናግረዋል። በቀን አንድ ዳቦ ብቻ እየተሰጠን በውሃ እጥረትም በአንድ ክፍል ውስጥ ታጭቀን እየተሰቃዬን እንገኛለን፤ አሁን ላይ ከበሽተኛ ይልቅ ጤነኞች ነው እየተጓዙ የሚገኙት ሲሉም ለአሚማ ገልጸዋል። እስረኞች አሁንም የበለጠ ትኩረት ተሰጥቷቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የሁሉም ድጋፍ እንዳይለያቸው ጥሪ አድርገዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply