በሳዑዲ አረቢያ ችግር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደአገራቸው መመለስ ጀመሩ። ባህርዳር:- መጋቢት 21/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በሳዑዲ አረቢያ ችግ…

በሳዑዲ አረቢያ ችግር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደአገራቸው መመለስ ጀመሩ። ባህርዳር:- መጋቢት 21/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በሳዑዲ አረቢያ ችግር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር በረራ ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች የአቀባበል ኮሚቴው አባላት ተገኝተዋል። በሳዑዲ አረቢያ የነበሩ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች እስከ ቀጣይ 11 ወራት ለመመለስ የተሰወነ ሲሆን፤ ለስደተኞች አቀባበልም ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ኮሚቴ መቋቋሙን ኢዜአ ዘግቧል። ስደተኞችን መልሶ እስኪቋቋሙ ድረስ ጊዜያዊ ማረፊያም መዘጋጀቱ ይፋ መደረጉ ይታወቃል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን: ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply