በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ተባለ

በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ።

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሴቶችና ህጻናት ፍትህ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተቀቋቋው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አካል የሆኑ ከፍተኛ አመራሮች ውይይት አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ እንደተገለጸው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በተቀናጀና ዘርፈ ብዙ በሆነ መንገድ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የህጻናት ፍትህን ለማረጋገጥ የተቋቋመ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት የሆኑ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሴቶች፣ሕጻናትና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ እንቁ አስናቀ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ጽሁፍ እንደተገለጸው በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የማስቀረትና መብታቸው እንዲከበር የመስራት ግዴታ የሁሉም ተቋማት ኃላፊነት ነው ተብሏል፡፡

በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መከላከልም ሆነ ተፈጽሞ ሲገኝ የተሟላ አገልግሎት መስጠት በፍትህ ተቋማት ብቻ የማይችል መሆኑ በመድረኩ ላይ መጠቆሙን ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።

ተጎጂዎቹ በጥቃቶቹ ምክንያት ከሚደርስባቸው ዘርፈ ብዙ የጤና፣ የስነልቦና፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማውጣትና መልሶ ለማቋቋም የሁሉም አካላት ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡

ጥቃትን ከመከላከልና ምላሽ ከመስጠት እንፃር እስከ አሁን ባለው ሂደት በተናጠል የመንቀሳቀስ እንዲሁም ወጥነትና ቀጣይነት የጎደለው አላስፈላጊ ድግግሞሽ መሰተዋሉ ተገምግሟል፡፡

በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ የሚታዩ ችግሮችን በየጊዜው እየፈቱ ለመሄድ እንዲሁም ሁሉም የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያግዝ ቅንጅታዊ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ስር የሰደዱ እና የተስፋፉ በመሆናቸው በተቀናጀና ዘርፈ ብዙ በሆነ መንገድ እርምጃዎችን መውሰድ በማስፈለጉ 19 አባል ተቋማትን ማለትም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ የጤና ጠበቃ ሚኒስቴር፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣች ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴርንና ሌሎች ተቋማትን የያዘ ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ  ተቋቁሞ ወደ ሥራ ተገብቷልም ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ተባለ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply