
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ እና ፖፑሌሽን ሰርቪስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የወደፊት ህይወታችውን ማግኘት በሚል በሴቶች ጤና አገልግሎትና በስነ ተዋልዶ ላይ የሚሰራ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።
የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ የፕሮጀክቱን ይፋ መሆን በገለጹበት ወቅት ÷ ባለፉት አመታት የቤተሰብ እቅድ ለማስፋፋት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በሀገራችን ካገቡ አፍላ ወጣቶች መካከል 22 በመቶ የሚሆኑት የተሟላ የቤተሰብ እቅድ እየፈለጉ አገልግሎቱንም ሆነ መረጃችን ማግኘት ያልቻሉ መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታው ጠቁመዋል።
ዶክተር ደረጀ አያይዘውም በሀገራችን ውስጥ ያሉ ሴቶች እና ልጃገረዶች ከማህበራዊ አድልዎ፣ ከአስገዳጅነት እና ከጥቃት በማላቀቅ ነጻ ፍትሀዊ ትክክለኛና በእውቀት ላይ የተመሰረተ የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ምርጫዎችን እንዲያገኙ በማስቻል በአፍላ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጃገረዶች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ከግባቸው ለመድረስ እንዲችሉ ሁሉም ዕድል ሊሰጣቸውና ሊደገፉ ይገባል ብለዋል።
የማሪ ስቶፕ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ ሽብሩ ፕሮጀክቱ የአፍላ ወጣቶችን ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ችግሮችን የሚፈታ ፣ ምላሽ ሰጪ እና ትምህርታቸውን ለማጠናቀቅ እድል የሚፈጥር አዲስ የጤና ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል።
ወጣት ላይ መስራት ኢትዮጵያን መገንባት ነው በማለት ማሪስቶፕስ ኢትዮጰርያ እና ፖፑሌሽን ሰርቪስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ለወጣቶች ትኩረት በመስጠት እየሰሩ ይገኛሉ ም ብለዋል።
ፕሮጀክቱም ከካናዳ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በጥምረት የሚተገበር መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የፕሮጀክቱ ዋነኛ ተጠቃሚዎች እድሜያቸው ከ15 እስከ 19 ዓመት የሆኑ በአፍላ ወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኙና ያገቡ ቢሆኑም በሁሉም የመውለድ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች፣ አጋሮቻቸውና እና ማህበረሰብ አባላት መረጃዎችንና አገልግሎቶችን የሚያገኙ ይሆናል ብለዋል።
ፕሮጀክቱም በሶስት ክልሎች በአስራ ሶስት ዞኖችና በሰላሳ ዘጠኝ ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
The post በሴቶች ጤና አገልግሎትና በስነ ተዋልዶ ላይ የሚሰራ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post