
#በስልክ የደረሰኝ አሳዛኝ መረጃ በትናንትናው ዕለት በምስራቅ ጎጃም ዞን በስናን ወረዳ ረቡዕ ገብያ ከተማ በመንግስት ወታደሮች ሶስት አርሶ አደሮች በግፍ ሲገደሉ እንድ አርሶ አደር ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ገጥሞታል። በረቡዕ ገብያ ከተማ ትናንት ማለዳ በርከት ያሉ ሚሊሻዎች እና ፖሊሶች በድንገት በመሰማራት ነው ተኩስ የከፈቱት ብሏል።በስልክ መረጃ ያደረሰኝ። የመንግስት ሚሊሻዎች እና ፖሊሶች እርምጃውን የወሰዱት አርሶ አደሩን የየዕለት ቀረጥ ካልከፈልክ በሚል እንደሆነ ገልጿልኛል።ከዚህ ቀደም የቁም ከብቶች ሲሸጡ እንደየመጠናቸው በየጊዜው ቀረጥ እንደሚከፍሉ ገልጿል።አሁን ግን መረጃ ሰጫችን እንደሚሉት ወደ ረቡዕ ገብያ ከተማ የሚገቡ የጋማ ከብቶች ሁሉ ለኮቴ ቀረጥ እንዲከፍሉ ታውጇል። ብሏል።ይህ ደግሞ አርሶ አደሩን እንዳስቆጣው ተገልጿል። አሁንም ችግሩ ወደለየለት የእርስ በዕርስ ዕልቂት ከማምራቱ በፊት ቁጭ ብለው በውይይት እንዲፈታ ጥሪ ቀርቧል። © ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናዉ
Source: Link to the Post