በስምንት ሰዓት ዉስጥ ብቻ 47ሺህ ብሎኬት ድረስ ማምረት የሚያስችል ፋብሪካ ስራ መጀመሩ ተገለፀ። ፋብሪካው በአንድ ፈረቃ (8 ሰዐት) ብቻ 47ሺ ባለ (40*10*20 ሳ.ሜ) ብሎኬቶችን የማም…

በስምንት ሰዓት ዉስጥ ብቻ 47ሺህ ብሎኬት ድረስ ማምረት የሚያስችል ፋብሪካ ስራ መጀመሩ ተገለፀ።

ፋብሪካው በአንድ ፈረቃ (8 ሰዐት) ብቻ 47ሺ ባለ (40*10*20 ሳ.ሜ) ብሎኬቶችን የማምረት አቅም እንዳለዉ ሰምተናል።

ቢውልደርስ አፕ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኑፋክቸሪንግ ኃ/ተ/ግ/ማ በከፍተኛ ጥራት የሚያመርታቸውን የብሎኬት እና ቴራዞ ምርቶች ለገበያ ማቅረብ መጀመሩን በፋብሪካዉ የፕሮጀክት ማናጀር እንዲሁም ባለድርሻ የሆኑት አቶ ወንደሰን መንገሰቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ማምረቻ ፋብሪካዉ 34 ሺ ባለ (40*15*20 ሳ.ሜ)፣ እና 25 ሺ ባለ (40*20*20 ሳ.ሜ)፣ ውፍረት/ስፋት ያላቸውን ብሎኬቶች የማምረት አቅም አለዉ ተብሏል፡፡

ቢውልደርስ አፕ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኑፋክቸሪንግ የሰለጠኑ ሀገራት የደረሱበትን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ 99 በመቶ ጥሬ ዕቃውን በአገር ውስጥ ግብዓት በመጠቀም እጅግ ዘመናዊ እና ጥራት ያለዉ ምርት ማምረት የሚችል የግንባታ ግብአት አቅራቢ ፋብሪካ ከኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት በተሰጠ ፍቃድ በዱከም ከተማ፣ ጠዴቻ ወረዳ አስገንብቶ ስራ አስጀምሯል።

በከፈተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የግምባታ ዘርፍ አለም አሁን በደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ለማገዝ አልሞ ባለፉት 18 ወራት የፋብሪካ ግምባታ እና ማሽን ተከላ ሲያከናውን መቆየቱን የሚገለሰፁት አቶ ወንደሰን
ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይወጣበታል ይላሉ።

ፍላጎትን መሰረት አድርገን በተጨማሪ ፈረቃ ምርት ማምረት እንችላለን ያሉት አቶ ወንደሰን በተመሳሳይ የቴራዞ ማምረቻው በተለያየ ሞልድ በቀን ከ 2500 ካ.ሜ በላይ የሚሸፍን ከፍተኛ ጭነት መቋቋም የሚችሉ የወለል ንጣፎችን ማምረት ይችላል ብለዋል፡፡

ይህ ፋብሪካ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ150 በላይ ዜጎች ቀጥተኛ የስራ እድል የሚፈጥር ሲሆን ምርት በብዛት በማምረት እና በማቅረብ በገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ማረጋጊያ ሚናን እንደሚጫወት ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply