በሶማሊያ ላይ የተጣለው የመሣሪያ ማዕቀብ እንዲነሳ ኢትዮጵያ ድጋፏን ገለጸች

https://gdb.voanews.com/80470000-c0a8-0242-a9dc-08daac945c1d_tv_w800_h450.jpg

ሶማሊያ የተጣለባትን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲነሳላት ለምታደርገው ጥረት ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ ስትሆን፣ ኢትዮጵያ ኡጋንዳን በመከተል ድጋፏን ገልጻለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ም/ቤት በመጪው ወር በሶማሊያ ላይ የተጣለውን ከፊል የመሳሪያ ማዕቀብ ለማራዘም ድምጽ ይሰጣል ተብሉ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ሶማሊያ ግን እስላማዊ አክራሪዎችን በተሻለ ለመዋጋት ትችል ዘንድ ማዕቀቡ መነሳት አለበት ባይ ነች።

የኢትዮጵያ ድጋፍ የመጣው ባለፈው ሃምሌ እስላማዊ አክራሪዎች ድንበሯን አልፈው ገብተው ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ እና ሶማሊያና ዓለም አቀፍ አጋሮቿ በአል-ሻባብ ላይ ከፍተኛ ጥቃት በማድረስ ላይ በሚገኙበት ወቅት ነው።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

Source: Link to the Post

Leave a Reply