በሶማሊያ በመኪና ላይ በተጠመደ ፈንጂ በደረሰ ጥቃት 21 ሰዎች ተገደሉ

https://gdb.voanews.com/c6f45109-6b03-4b1b-ad53-c61800e821bb_w800_h450.jpg

በማዕከላዊ ሶማሊያ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ በተፈጸመው በመኪና ላይ በተጠመደ የቦምብ ጥቃት፣ የሞቱት ሰዎች ብዛት 21 እንደደረሰ እየተነገረ ይገኛል።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች፣ አሁንም ፍንዳታው ካስከተለው ፍርስራሽ ውስጥ አስከሬኖችን በማውጣት ላይ እንደኾኑ ተዘግቧል።

አንድ አጥፍቶ ጠፊ ሲያሽከረክረው የነበረው ቦምብ የተጫነ መኪና፣ የፍተሻ ኬላን አልፎ እንደገባ ሲፈነዳ፣ በአካባቢው የነበሩ ሕንፃዎችን ማፈራረሱንና በዚኽም በደርዘን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች እንደተጎዱ ተመልክቷል።

ጥቃት አድራሹ፣ ሰዎች በብዛት የሚገኙበትን የመኖሪያ እና የሥራ አካባቢን ዒላማ አድርጎ እንደነበር፣ የአካባቢው ፖሊስ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል አስታውቋል።

ቅዳሜ ዕለት ለደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት፣ ወዲያውኑ ሓላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሳን ሼክ ሞሐመድ ጥቃቱን አውግዘው፣ ለ15 ዓመታት አገሪቱን ሲያተራምስ ቆይቷል ያሉትን አል-ሻባብን እንደሚደመስሱ ዝተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply