በሶማሊያ በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሞ የነበረው ሰው በአንድ ወቅት የአልሸባብ ተዋጊ በኃላም የሶማሊያ ጦር አባል እንደነበር ተነገረ፡፡በሞቃዲሾ የሚገኘውን ወታደራዊ ካምፕ በማጥቃ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/jcbiYD9rgCqM_Tk_v5Jx_9p_dkSKioFpuFFkw0jgO8nXZrKTQOa4XBBncoNaWgYKlJbF_nuNN8VgFMMs-0bNudian9Wo1fkMxt5Q38JsSog0t_Lmb5gU1OoR0Shwxe0HOuje3AhsF4i5uRGd2FksvSn2jnL7OmmyyKZEOF9QDDofvCU50sn5F_vvEMSst7wW16YTbguMDMEJi-1UMWORoVInSeVOnVJ1ZAD6jJzladr5o0GWFBwZy-yAw3NdCoX4pOcKlRYVmYF9oQootCB3cCdmFEKJlWBm3zqd4AcvKZUQYKpJlFizWbTCyAsQUKxv3tmSGNg8FfLinNNIkKwPbw.jpg

በሶማሊያ በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሞ የነበረው ሰው በአንድ ወቅት የአልሸባብ ተዋጊ በኃላም የሶማሊያ ጦር አባል እንደነበር ተነገረ፡፡

በሞቃዲሾ የሚገኘውን ወታደራዊ ካምፕ በማጥቃት አምስት የውጭ ሀገር ወታደሮችን የገደለው ወታደር የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን የቀድሞ አባል እንደነበር ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገቧል።

ጥቃት ፈጻሚው በሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ወታደር ሆኖ ከመመለመሉ በፊት ከአልሸባብ መውጣቱን በርካታ ምንጮች ዘግበዋል።

በሠራዊቱ ወታደሮች ምልመላ ሂደት ላይ ጥብቅ የሆነ የኋላ ታሪክ አለመኖሩን ድርጊቱ አጋልጧል።

በጎሳ ላይ የተመሰረተ አድሎአዊነት፣ ሙስና እና አቅም ማነስ ወጣቶች ታጣቂ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ምክንያቶች መሆናቸውን የሶማሊያ የዜና አውታር ጋሮዌ ኦንላይን ዘግቧል።

በጄኔራል ጎርደን ወታደራዊ ካምፕ ከተገደሉት አምስት ወታደሮች መካከል አራቱ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ሲሆኑ አንደኛው የባህሬን ነው።

የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply