በሶማሊያ በደረሰ ፍንዳታ በስፍራው የነበሩ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ፡፡

በሶማሊያ በፓርላማ አካባቢ በደረሰ የመኪና ላይ ፍንዳታ በቦታው የነበሩ ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡በመዲናዋ ሞቃዲሾ የሶማሊያ ፓርላማ አቅራቢያ በሚገኝ የፍተሻ ጣቢያ አቅራቢያ ፍንዳታው መከሰቱ የተነገረ ሲሆን በፍንዳታውም ቢያንስ ሶስት ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ እና ስምንት ሰዎች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ነው የተነገረው፡፡

ፍንጁ ተጠምዶበት የነበረው መኪና በዋና ከተማዋ የሚገኘውን የፍተሻ ጣቢያ ጥሶ መግባቱን የአይን እማኞች መግለፃቸው ተነግሯል፡፡በየጊዜው ፍንዳታ የማያጣት ሶማሊያ የካቲት 8 ምርጫ ልታካሂድ የነበረ ቢሆንም በድምፅ አሰጣጡ ላይ ስምምነት ባለመደረሱ መራዘሙም ይታወቃል፡፡

ለደረሰው ጥቃትም እስካሁን ሃላፊነቱ የወሰደ አካል ባይኖርም የአልቃይዳ ክንፍ የሆነው እና በከተማዋ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡በከተማዋ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ አሸባሪ ቡድን ምርጫ የሚደረግ ከሆነ በምርጫ ጣቢያዎች ላይም ጥቃት እፈፅማለሁ ማለቱን የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡

ቀን 08/06/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply