በሶማሊያ ቢያንስ 20 ሰዎች በአጥፍቶ ጠፊዎች በመኪና ላይ ባደረሱት ፍንዳታ ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ በትናንትናው እለ…

በሶማሊያ ቢያንስ 20 ሰዎች በአጥፍቶ ጠፊዎች በመኪና ላይ ባደረሱት ፍንዳታ ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በትናንትናው እለ…

በሶማሊያ ቢያንስ 20 ሰዎች በአጥፍቶ ጠፊዎች በመኪና ላይ ባደረሱት ፍንዳታ ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በትናንትናው እለት የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በመዲናዋ ሞቃዲሾ ወደብ አቅራቢያ ከሚገኘው ምግብ ቤት በአጥፍቶ ጠፊዎች አማካኝነት በደረሰው የመኪና ላይ ፍንዳታ ከ 20 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ኢኤፍ የተሰኘው የዜና ወኪል ገልጧል።ሌሎች 30 ሰዎች ቆስለዋም ብሏል። ፍንዳታው ወደቡ አቅራቢያ በሚገኘው የሉኡል የመን ምግብ ቤት ውስጥ ተከስቷል። ባለሥልጣኑ ሞሃመድ ኦስማ ፍንዳታው በጣም ጠንካራ እና ከፍተኛ ውድመት ያስከተለ ሲሆን በሰላማዊ ዜጎች ላይም ጉዳት አድርሷል ብለዋል ፡፡ ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን የለም ግን ሀገሪቱ ከአልቃይዳ ጋር ተያያዥነት ባላቸው የአልሸባብ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶች እየደረሱባት ነው፡፡ ቡድኑ በመላው አፍሪካ ቀንድ ሀገር ሁከትና ዓመፅ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ የቡድኑ ታጣቂዎች በ 2011 በ 20 ሺህ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በተደገፉ የመንግስት ወታደሮች ከሞቃዲሾ እንዲባረሩ መደረጋቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ቡድኑ አሁንም ከከተሞች ውጭ ሰፊ ቦታዎችን በመቆጣጠር በመንግስት አካላትና ተቋማት ላይ ኢላማ አድርገው ጥቃት የሚሰነዝሩ ታጣቂዎችን አሰማርቷል፤ አልፎ አልፎም ድንበር አቋርጦ በኬንያ ወረራዎችን ያካሂዳል፡፡ ከ 1991 አንስቶ ሶማሊያ ውስን የማዕከላዊ መንግስት ብቻ ያላት በመሆኗ በተባበሩት መንግስታት ድጋፍ እራሷን እንደገና ለመገንባት እየሞከረች ነው፡፡ የዘገባ ምንጭ_አፍሪካን ኒውስ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply