በሶማሊያ አንድ ሚሊየን ዜጎች በድርቅ ምክንያት ከቀያቸዉ ተፈናቀሉ፡፡በሶማሊያ የተከሰተዉ ታሪካዊ ድርቅ አንድ ሚሊዮን ዜጎች ቀያቸዉን ለቀዉ እንዲፈናቀሉ ማድረጉንና አገሪቷን በረሀብ ጥላ ዉ…

በሶማሊያ አንድ ሚሊየን ዜጎች በድርቅ ምክንያት ከቀያቸዉ ተፈናቀሉ፡፡

በሶማሊያ የተከሰተዉ ታሪካዊ ድርቅ አንድ ሚሊዮን ዜጎች ቀያቸዉን ለቀዉ እንዲፈናቀሉ ማድረጉንና አገሪቷን በረሀብ ጥላ ዉስጥ እንድትወድቅ ማድረጉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታዉቋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ እና የኖርዌይ የስደተኞች ኤጀንሲ ከ 755 ሺህ በላይ ዜጎች ቤታቸዉን ለቀዉ በድንበሮች አቅራቢያ ከተቀመጡትና አገራቸዉን ለቀዉ ከተሰደዱት ጋር ሲደመር አንድ ሚሊዮን እንደሚደርስ ነዉ ያስታወቀዉ፡፡

ሶማያሊያ እና የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ኬንያ፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ባለፉት አራት የተዛባ የዝናብ ወቅቶች ከብቶችና ሰብሎች ማለቃቸዉን ተከትሎ በከባድ ድርቅ መመታታቸዉ ይታወሳል፡፡
የተዛባዉ የዝናብ ወቅት ብዙ ዜጎችን ከመንደራቸዉና ከቀያቸዉ አፈናቅሏል ብሏል፡፡
#ቢቢሲ አፍሪካ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 06 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply