በሶማሌ ክልል ከ21 ቢሊዮን በላይ ሜትር ኪዩቢክ የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ ተረጋገጠ

በሶማሌ ክልል ኦጋዴን በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ መረጋገጡን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ እንዳስታወቁት፤ በሶማሌ ክልል ኦጋዴን በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

በአካባቢው 19 ጉድጓዶችን በመቆፈር በተደረገ ዳሰሳ የተፈጥሮ ጋዙ የተገኘ ሲሆን ወደፊት ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠል ከቻለ አሁን ከተገኘው እጥፍ በላይ ማግኘት እንደሚቻል የሚጠቁሙ መረጃዎች እንዳሉ ሚኒስትር ዴኤታው አመላክተዋል፡፡

በክልሉ የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ በቅርብ ዓመታት ወደ ምርት ለማስገባት ሰፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን እና ሌሎች በፍለጋ ምዕራፍ ላይ ያሉትም በአጭር ጊዜ ውጤታማ እንደሚሆሙ ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ በስድስት ቦታዎች ላይ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት አለ የተባለ ሲሆን ኦጋዴን፣ መቀሌ፣ መተማ፣ ደቡብ ኦሞ እንዲሁም ጋምቤላ አካባቢዎች በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸው ተገልጿል። በአካባቢዎቹ ላይ የተጀመሩ የፍለጋ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply