በሶማሌ ክልል የጀረር ዞን የአቦኮር ነዋሪዎች መንግስት እየካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ በመደገፍ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን ገለፁ

በሶማሌ ክልል የጀረር ዞን የአቦኮር ነዋሪዎች መንግስት እየካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ በመደገፍ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በሶማሌ ክልል የጀረር ዞን የአቦኮር ቀበሌ ነዋሪዎች መንግስት እየካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ በመደገፍ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን ገለፁ።
በሶማሌ ክልል የተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎችን እየጎበኙ የሚገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ መስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በጀረር ዞን አቦኮር ቀበሌ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ነዋሪዎቹ የህወሃት ቡድን ህዝቡን ለዘመናት ሲገድሉ እና ሲያሰድዱ መኖራቸው ሳያንስ ስልጣን ከእጃችን ከወጣ አንኖርም በሚል በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሱትን ክህደት እና ጭፍጨፋ እናወግዛለን  ብለዋል።
ነዋሪዎቹ ሁልግዜም ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሚቆሙም ማረጋገጣቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ከፍተኛ ሃላፊዎች ከነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ብሎም በሰላም እና ልማት ዙሪያም ውይይት አድርገዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በቀበሌው በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህር ቤት በመገኘት የማስፋፊያ ፕሮጀክቱን አስመርቋል።

The post በሶማሌ ክልል የጀረር ዞን የአቦኮር ነዋሪዎች መንግስት እየካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ በመደገፍ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን ገለፁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply