በሶስት ቢሊዮን ብር ካፒታል የአዲስ አበባ የንግድ ስራዎች ድርጅት መቋቋሙ ተገለፀ፡፡በከተማዋ የተፈጠረውን የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣምና እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር ያስችላል…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/tta1DuEHYgpbW_az7SNFVF4i3IicqCB9l1DMGMbPR0YFkZtC07Wnc9t_0KfYL1fV4R05vk862Ym2ARFCf2ctZsOw1KKcahKYoS6VhjFVNQalYfVZ_kIbiZ6-_spmrxHwwifRxuHu1ipJYThPOS1l1psujOQAYirU14jth_Sleety7OvkaFXfHqZRPuiNtVUO06d4TLW4FK4xI5_lZpwluqjXq9FhtybA7VfNu7CQ5SK_-YIwd7UqHHwtcNfi3y6kOTqWYId_F4DXyeN2-7OizpXs3KmAiEjq7n1HR8NFSHGIjQXdexHGRK2U8seL0dKWpA0LCm5ZIHfoVSWBvOrwNg.jpg

በሶስት ቢሊዮን ብር ካፒታል የአዲስ አበባ የንግድ ስራዎች ድርጅት መቋቋሙ ተገለፀ፡፡

በከተማዋ የተፈጠረውን የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣምና እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለለት የመንግስት የልማት ድርጅት መቋቋሙ ተገልፃል፡፡

አቶ ጀማል ሳላህ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ የህግ ጥናትና ምርምር ረቂቅ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳስታወቁት የከተማው አስተዳደር ለከተማ ነዋሪው በተፈጠረው የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር እና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎች የግብርና እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምርቶችን እና የንግድ ዕቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በቀጥታ ከአርሶ አደሩ በመግዛት የሚያቀርብ ድርጅት መቋቋሙን ነግረውናል፡፡

የልማት ድርጅቱ ተጠሪነት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ መሆኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ የግብርና እና የኢንዲስቱሪ ምርቶች ዋጋ እየጨመረ በመምጣቱና ህብረተሰቡ ለኑሮ ውድነት ከፍተኛ ተጋላጭ በመሆኑ ይህ ደንብ መውጣቱን አስታውቀዋል፡፡

የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ቅርንጫፍ ሊኖረው እንደሚችልም ተገልፃል፡፡
የልማት ድርጅቱ በሶስት ቢሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን የሚቆይበት ግዜ እንደማይታወቅ ዳይሬክተሩ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ጥቅምት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply